ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለውን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ወደ ኢምባሲ አሳድጋለች?
በሀርጌሳ የኢትዮጵያ ቆንሱላ ልዑክ የነበሩት ደሊል ከድር ከሰሞኑ የአምባሳደርነት ሹመት ማግኘታቸው ይታወሳል
በአረብ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚኖሩ መካከል ከ27 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ተብሏል
ኢትዮጵያ በሀርጌሳ ያለውን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ወደ ኢምባሲ አሳድጋለች?
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ፤ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ባሉ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ከጋዜጠኞች ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጉዳይ ዋነኛው ነበር፡፡
ሶማሊላድ ከሰሞኑ ኢትዮጵያ በሀርጌሳ የሚገኘውን ቆንሱላ ጽህፈት ቤት ወደ ኢምባሲ ማሳደጓን ይፋ ያደረገች ሲሆን ኢትዮጵያም በጉዳዩ ዙሪያ በይፋ ምላሽ ሳጥሰጥ ቆይታለች፡፡
እውን ኢትዮጵያ የሀርጌሳ ቆንሱላ ጽህፈት ቤቷን ወደ ኢማባሲ አሳድጋለች? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ አምባሳደር ነብዩ በቀጥታ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ለጉዳዩ በሰጡት ቀጥተኛ ያልሆነ ምላሽ ኢትዮጵያ በሀርጌሳ የኢትዮጵያ ቆንሱላ ጽህፈት ቤት ልዑክ ሆነው እያገለገሉ ያሉት ደሊል ከድር በአምባሳደርነት ከመሾማቸው ውጪ የምጨምረው ነገር የለኝም፣ ስለዚህ ጉዳይ ለመናገርም ስልጣኑ የለኝም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አምባሳደር ነብዩ አክለውም ከሰሞኑ በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአምባሳደርነት ከተሾሙት ውስጥ አንዱ አምባሳደር ደሊል ከድር በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ውስጥ ረጅም ጊዜ ሲሰሩ የነበሩ ዲፕሎማት ናቸውም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሄ አብዲ ከአራት ወራት በፊት በወደብ ጉዳይ በአዲስ አበባ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው ይታወሳል።
ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ በኪራይ የወደብ ባለቤት እንድትሆን ሶማሊላንድ ደግሞ የሀገርነት እውቅና እንድታገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ሶማሊላንድን የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ በምታያት ሶማሊያ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን እና ተቃውሞን አስከትሏል።
አሜሪካ በመላው ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም እንዲታወጅ ጠየቀች
ከአንድ ወር በፊት ሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደርን በ72 ሰዓት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ እና በሀርጌሳ እና ጋሮዌ ያሉ የኢትዮጵያ ቆንሱላ ጽህፈት ቤቶች እንዲዘጉ ሰራተኞቹም በሁለት ሳምንት ውስጥ ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን አስታውቃ ነበር፡፡
በወቅቱም ራስ ገዟ ሶማላንድ እና ፑንት ላንድ የሶማሊያ መንግስት በሀርጌሳ እና ጋሮዌ የሚገኙ ቆንስላዎች እንዲዘጉ ያሳለፈውን ውሳኔ መቃወማቸው አይዘነጋም።
ሶማሊያ በሀርጌሳ ያለው እና እንዲዘጋ ስትል ውሳኔ ያሳለፈችበት የኢትዮጵያ ቆንሱላ ጽህፈት ቤት ወደ ኢምባሲ አድጓል በሚል ሰሞንኛው ጉዳይ ዙሪያ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡
ሌላኛው ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጉዳይ ሲሆን በዚህም ከሚያዝያ ወር ጀምሮ 27 ሺህ 57 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡