ፖለቲካ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው ከኃላፊነት ተነሱ
አቶ መንግስቱ ንጉሴን ደግሞ የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርነት ተሾመዋል
የዓለም ሲቪል አቪዬሽን ም/ ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ የነበሩት አቶ ጌታቸው መንግስቴ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ተደርገው ተሾመዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ካናዳ ሞንትሪያ በሚገኘው የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ምክር ቤት የኢትዮጵያ ተወካይ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩትን አቶ ጌታቸው መንግስቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አቶ ጌታቸው መንግስቴ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር፤ አቶ መንግስቱ ንጉሴን ደግሞ የኤር ናቪጌሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ተቋሙ አስታውቋል።
አቶ ጌታቸው መንግስቴ፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ረዘም ላለ ጊዜ ተቋሙን በዋና ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛውን በመተካት ነው።
aXA6IDMuMTQyLjE5Ny4xOTgg
ejasoft island