ኦሚክሮን ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ በዓለም ላይ ከ4 ሺ 500 በላይ በረራዎች ተሰረዙ
የተሰረዙት በረራዎች ለገና ዋዜማ እና በዓል ወቅት ለማድረግ የታቀዱ ነበሩ
ከዚህ በተጨማሪም ከ10 ሺህ በላይ በረራዎች መዘግየታቸውም ተነግሯል
ኦሚክሮን ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ በዓለም ላይ ከ4 ሺህ በላይ በረራዎች ተሰረዙ፡፡
ኦሚክሮን የተሰኘው አዲሱ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ መከሰቱን ተከትሎ መነቃቃት አሳይቶ የነበረው ቱሪዝም እና የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ለዳግም ስጋት ተዳርጓል፡፡
ከሁለት ዓመት በኋላ የገና በዓል በድምቀት እንደሚከበር ታስቦ የነበረ ቢሆንም አዲሱ የኮቪድ ልውጥ ዝርያ በተለይም በአውሮፓ አገራት ክትባት ገና ደብዝዞ እንዲከበር ምክንያት መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
በአውሮፓ አስከ ቀጣዩ የካቲት ድረስ 500 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ተባለ
ለገና በዓል በሚል አስቀድመው የታቀዱ ጉዞዎች እና በረራዎች አገራት ዜጎች ወደ አደባባይ እንዳይወጡ እገዳ መጣላቸውን ተከትሎ መንገደኞች የበረራ እቅዶቻቸውን ሰርዘዋል፡፡
የዓለማችንን አቪዬሽን እንቅስቃሴዎችን ተከታትሎ በመዘገብ የሚታወቀው ፍላይት አዌር የተሰኘው ተቋም በድረገጹ ባወጣው ሪፖረት መሰረት በፈረንጆቹ ገና ዋዜማ እና በዓሉ እለት ማለትም ትናንት እና ዛሬ ብቻ 4 ሺህ 500 ዓለም አቀፍ በረራዎች ተሰርዘዋል፡፡
‘ኦሚክሮን’ ቫይረስ በመላው ዓለም ከፍተኛ ስጋትን ደቅኗል- የዓለም ጤና ድርጅት
ከዚህ በተጨማሪም ከ10 ሺህ በላይ በረራዎች ደግሞ ለበርካታ ሰዓታት የዘገዩ ሲሆን ክስተቱ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
ከተሰረዙ እና ከዘገዩ በረራዎች መካከል ሩብ ያህሉ የአሜሪካ የንግድ አየር መንገዶች እንደሆኑ የዚሁ ተቋም ሪፖርት ያሳያል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ዴልታ አየር መንገዶች ብቻ 280 በረራዎችን የሰረዙ ሲሆን በርካታ አገራት የጉዞ እገዳ ማስተላለፋቸው ለበረራዎቹ መሰረዝ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡
ኦሚክሮን በአውሮፓ እና አሜሪካ በፍጥነት እየተሰራጨ ሲሆን አሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 197 ሺህ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ተጠቅተዋል፡፡
በተለይም ኒዮርክ፣ ሚቺጋን፣ ኢንዲያና እና ኦሃዮ ግዛቶች ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋባቸው አካባቢዎች ናቸው፡፡
እንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ አገራት በዚሁ አዲስ ቫይረስ ክፉኛ የተጠቁ ሲሆን በለንደን ካሉ 20 ነዋሪዎች ውስጥ አንዱ በኮሮና ቫይረስ እንደተጠቃ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡