ድሪቤ ወልተጂ በ1 ማይል የጎዳና ላይ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች
በሴቶች በ1 ማይል የጎዳና ላይ ሩጫ ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳሊያ አገኘች
የዓለም የመጀመሪያ የዓለም የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውደድር በላቲቪያ ሪጋ እየተካሄደ ነው
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ድርቤ ወልተጂ ወልተጂ በ1 ማይል የጎዳና ላይ ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች።
በላቲቪያ ሪጋ በተደረገው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ በሴቶች 1 ማይል የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ አትሌት ድሪቤ ወልተጂ እና አትሌት ለምለም ኃሉ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጠናቀዋል።
አትሌት ድርቤ ወልተጂ ርቀቱን 4 ደቂቃ ከ21 ሰከንድ በመግባት በርቀቱ የከክብረ ወሰን ባለቤት መሆኗን ዎርልድ አትሌቲክስ አስታውቋል።
የዓለም የመጀመሪያ የዓለም የጎዳና ላይ የአትሌቲክስ ውደድር በላቲቪያ ሪጋ እየተካሄደ ነው።
- ትዕግስት አሰፋ በበርሊን የማራቶን ሪከርድ የሰበረችበት ልዩ ጫማ
- በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከተሳተፉ 195 ሀገራት ሜዳሊያ ያገኙት 46ቱ ብቻ ናቸው
ቀደም ብሎ በተካሄደው የወንዶች 5ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያኑ አትሌት ሀጎስ ገብህይወት እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልጃ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የብር እና የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝተዋል።
የሴቶች 5ኪ.ሜ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 14:40 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
ኢትዮጵያ ዛሬ ረፋድ በተጀመረው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ እሰካሁን 2 የወርቅ፣ 2 የበር እና አንድ የነሃስ በድምሩ 5 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችላለች።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉበት ውድድሮቸ ቀጥለው እየተካሄዱ ይገኛሉ።