በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ዜግነትን የአፍሪካ ህብረት ይፋ አድርጓል
በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ዜግነትን የአፍሪካ ህብረት ይፋ አድርጓል
ዝርዝሩን ይፋ ያደረገው አፍሪካ ህብረት ነው፡፡ በአፍሪካ እስካሁን 26 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከነዚህም መካከል 17ቱ አልጀሪያውያን ናቸው፡፡ ከቻይና ውሀን ግዛት የተነሳው ኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ፍጥነት በመስፋፋት እስካሁን ከ60 በላይ ሀገራትን ማዳረስ ችሏል፡፡
በቫይረሱ ምክንያት እስካሁን በቻይና 2,984 ሰዎች ሲሞቱ፣ከቻይና ውጭ ደግሞ 254 ሰዎች መሞታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ የቫይረሱ መስፋፋት ያሳሰበው የአለም ባንክ በቫይረሱ የተጠቁ ሀገራት በሽታውን መከላከል እንዲችሉና የበሽታውን አስከፊ ተጽእኖ መቀነስ እንዲችሉ 12 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን በትናንትናው እለት ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡