አዲሱ የአሜሪካ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅ የማይወልዱ ሴቶችን የወረፉበት ንግግር ቁጣን ቀስቅሷል
የዶናልድ ትራምፕ አጣማሪ ጄዲ ቫንስ ልጅ የማይወልዱ ሴቶችን ተችተዋል
ጂዲ ቫንስ "ንግግሬ ስህተት ነበር ይቅርታ እጠይቃለሁ" ብለዋል
አዲሱ የአሜሪካ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ልጅ የማይወልዱ ሴቶችን የወረፉበት ንግግር ቁጣን ቀስቅሷል።
የፊታችን ህዳር ወር ላይ እንደሚኬሄድ የሚጠበቀው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሁንም ትኩረት እንደሳበ ነው።
በዚህ ምርጫ ላይ ሪፐብሊካን ፓርቲን ወክለው የዶናልድ አጣማሪ የሆኑት ጄዲ ቫንስ በተፈጥሯቸው ልጅ መውለድ እየቻሉ ነገር ግን የማይወልዱ ሴቶችን የወረፉበት ንግግራቸው ቁጣን ቀስቅሷል።
እጩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ልጅ አልባ በሆኑ ፖለቲከኞች እየተመራች ነው ብለዋል።
የቫንስ ንግግር በቀጥታ ልጅ ላልወለደችው እና የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስን የሚመለከት ነው ቢባልም ሌሎች ሴቶችም ንግግሩን ተችተዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ጆ ባይደንን በመተካት የአሜሪካ ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ለመሆን እና የፓርቲው ዋነኛ ዕጩ ለመሆን እየተወዳደሩ ያሉት ካማላ ሀሪስ ባለትዳር ቢሆኑም እስካሁን ልጅ አልወለዱም።
የሶስት ልጆች አባት የሆኑት ጄዲ ቫንድ ካማላ ሀሪስን ለማጥቃት በሚል ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ልጅ አልባ ፖለቲከኞች ራሳቸውን ጨምሮ አሜሪካን እየጎዱ ነው ያሉት ንግግር ትችት አስከትሎባቸዋል።
እጩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ከሶስት ዓመት በፊት ከአንድ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ቃለ መጠይቅ አድርገውም ነበር።
ለዓመታት ሲተላለፍ የነበረው ፍሬንድስ ተከታታይ ፊልም ላይብበመተወን የምትታወቀው ጀኒፈር አኒሰተን የጄዲ ቫንስን ንግግር ከተቹት መካከል ዋነኛዋ ናት።
በአሜሪካ ልጅ አለመውለድ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የምትናገረው ተዋናኝ አኒስተን የቫንስ አስተያየት ችግሩን እንደሚያባብስ ተናግራለች።
ቫንስ በበኩሉ ንግግሩ ልጅ ሙውለድ እየቻሉ መውለድ የማይፈልጉ ፖለቲከኞችን እንጂ በተፈጥሮ ልጅ መውለድ ያልቻሉትን አይደለም ብሏል።
"አውቃለሁ ስህተት ሰርቻለሁ፣ ይቅርታ እጠይቃለሁ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።
የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ሊቀመንበር ክሪስ ላሲቪታ በበኩላቸው " በቫንስ ንግግር ምክንያት በዕጩነታቸው ላይ የሚቀየር ነገር የለም፣ ትራምፕ ቫንስን ይወዱታል" ሲል ተናግራል።