ካማላ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ሆነው ቢቀርቡ አጣማሪዎቻቸው እነማን ሊሆኑ ይችላሉ?
ፕሬዝደንት ባይደን በትናትናው እለት በመጭው ህዳር ወር ከሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ አድርገዋል።
ራሳቸውን ከምርጫ ያገለሉት ባይደን ምክትላቸው ካማላ ሀሪስ እጩ ሆነው እንዲቀርቡ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል
ካማላ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ሆነው ቢቀርቡ አጣማሪዎቻቸው አነማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቶች ወጥተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ባለፈው ወር ከሪፐብሊካኑ ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በነበራቸው ክርክር ደካማ አፈጻጸም ካሳዩ በኋላ ዲሞክራቶች ራሳቸውን ከእጩነት እንዲያገሉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር።ባይደንም ለጫናው እጃቸውን ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንት ባይደን በትናትናው እለት በመጭው ህዳር ወር ከሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ አድርገዋል።
ባይደን በእሳቸው ቦታ ምክትላቸው ካማላ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ፕሬዝደንት ሆነው እንዲቀርቡ ሙሉ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
የባይደንን ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን ተከተትሎ ሀሪስ የዲሞክራት እጩ ሆነው ይመረጣሉ የሚል ከተፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል።
ከህንዳዊት እናት እና ከጀማይካዊ አባት የተወለዱት ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፓርቲያቸውን ይወክሉ ዘንድ የበርካታ ዴሞክራቶችን ድጋፍ አግኝተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ካማላ እጩ ሆነው ከበቀረቡ በምርጫው በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሊያጣምሯቸው የሚችሉ እጩዎች ዝርዝር ወጥቷል፡፡
የኪንታኪ ግዛት ገዢ ኤንዲ ቢሽር የካማላ አጣማሪ እንደሚሆኑ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ቀዳሚው ናቸው፡፡
በርካታ የሪፐብሊካን ደጋፊዎች በሚገኙበት ኪንታኪ ግዛት በማስተዳደር ላይ የሚገኙት ቢሽር በሪከርድ የተመዘገበ የስራ እድል በመፍጠር ፣ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን አቅም እና ጥራት በማጠናከር እንዲሁም የጤና ሽፋንን በማስፋት መልካም የሚባል የስራ አፈጻጸም ያላቸው ናቸው፡፡
ኤንዲ ቢሽር በግዛቷ ምክር ቤት የወጣውን ውርጃን የሚከለክለውን ህግ በመሻርም ይታወቃሉ፡፡
በአሁኑ ወቅት የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚንስትር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ፒት ቡቲጄጅ ሁለተኛው ከፍተኛ ግምት ያገኙ እጩ ናቸው፡፡
በ2020 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ በነበራቸው ተሳትፎ በዴሞክራት ፓርቲ ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኙት ፒት በ2021 በተመሰረተው የባይደን ካቢኔ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተሹመዋል፡፡
የቀድሞው የኢንዲያና ከንቲባ የነበሩት እኚህ ሰው ህዳር ላይ ለሚደረገው ምርጫ በሚቺጋን ግዛት ያላቸው ተቀባይነት ለዴሞክራቶች ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡
የአሪዞና ግዛት ሴናተር ማርክ ኬሊይ ሌላኛው የካማላ ሃሪስ አጣማሪ እንደሚሆኑ ከሚጠበቁ ብርቱ እጮዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የቀድሞው የአሜሪካ ባህር ሃይል ካፒቴን እና ጠፈርተኛ ማርክ ኬሊይ በወታደራዊ አገልግሎታቸው እና በለዘብተኛ አቋማቸው በሁለቱም ፓርቲዎች ዘንድ የሚከበሩ ሰው እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡
ባለቤታቸው ጋብሪየላ ጊፎርድ በርካታ ሰዎች በሞቱበት የ2011ዱ የጦር መሳሪያ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በዚህ የተነሳም ዴሞክራቶች በዚህኛው ምርጫ ልዩ ትኩረት አድርገው ከሚቀሰቅሱባቸው የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ጉዳይ ላይ ከግላዊ ተሞክሯቸው በመነሳት በርካታ ድጋፎችን ሊያሰገኙላቸው እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ሶስት እጩዎች ከፍተኛ ግምትን በማግኝት ቀዳሚ ቢሆኑም የካማላ ሃሪስ አጣማሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምት የተሰጣቸው አጠቃላይ እጩዎች ቁጥር ስምንት መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል