ሐኪሞች 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከአንድ ሰው ሆድ ውስጥ በቀዶ ጥገና አስወገዱ
ሐኪሞቹ እባብ መሳይ ፍጥረቱን ያወጡት በቀዶ ጥገና ከነ ህይወቱ ነው ተብሏል
ግለሰቡ በተደጋጋሚ ሆዱን ይቆርጠው እንደነበር ተናግሯል
ሐኪሞች 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከአንድ ሰው ሆድ ውስጥ በቀዶ ጥገና አስወገዱ፡፡
የ34 ዓመቱ ቬትናማዊ ሆዱን በተደጋጋሚ ቁርጠት ህመም ሲሰማው እና ማስታገሻዎችን ቢወስድም መሻሻል ባለማየቱ ነበር ወደ ሆስፒታል ያመራው፡፡
ያመራበት ሐኪሞች ባደረጉለት ምርመራም በሆዱ ውስጥ መጠኑ ባልተለመደ መልኩ ከፍ ያለ ተንቀሳቃሽ አካል መኖሩን ይነግሩታል፡፡
ቀጥሎ በተደረገለት የቀዶ ህክምና መሰረትም 30 ሴንቲ ሜትር ርዝመት ያለው እባብ መሳይ ፍጥረት ከሆዱ ውስጥ እንደወጣለት ተገልጿል፡፡
ከነ ህይወቱ በቀዶ ጥገና የወጣው ይህ አባብ መሳይ ፍጥረት የታካሚውን አንጀት ሲጎዳው እንደቆየ፣ ለቁርጠት እና ሌሎች ህመሞች ሲዳርጉት ነበር ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በራሱ ጭንቅላት ላይ ቀዶ ጥገና ያደረገው ሩሲያዊ
ይህን መያህል መጠን ያለው አካል እንዴት በሆድ ውስጥ ሊኖር ቻለ የሚለው ጥያቄ እስካሁን ያልተመለሰ ሲሆን ምን አልባት ይህ እባብ መሳይ ፍጥረቱ በግለሰቡ መቀመጫ በኩል ሊገባ እንደሚችል ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡
ቀስ በቀስም ወደ አንጀቱ እና ሆድ እቃው ውስጥ ሊንቀሳቀስ እና ሊኖር እንደቻለም ሐኪሞቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ግለሰቡ አሁን ላይ በመልካም ጤንነት ላይ ነው የተባለ ሲሆን ተጨማሪ የሆድ እቃ ጉዳት መኖር አለመኖሩን ክትትል እየተደረገለት ነውም ተብሏል፡፡