አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች ላይ የፈፀመችውን ስህተት የሚያሳይ ሰነድ ወጣ
ለተፈፀሙ ስህተቶች ግን አስካሁን ተጠያቂ የተደረገ አካል የለም ተብሏል
አሜሪካ በአየር ድብደባዎችቹ ወቅት በፈፀመቸቻው ስህተቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን መሞታውን ሰነዱ አመላክቷል
አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች ላይ የፈፀመችውን ስህተት የሚያሳይ ሰነድ ከሰሞኑ ይፋ ሆኗል።
በቅርቡ ከአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጎን እንደወጣ የተነገረለት ሰነድ አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ባካሄደቻቸው የአየር ድብደባዎች በርካታ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የሚያመላክት ነው።
በስህተት ተፈጽመዋል በተባሉት የአየር ድብደባዎቹም ህይወታቸው ካለፈ ንጹሃን ዜጎች መካከል በርካታ ህጻናት እንደሚገኙበትም ተመላክቷል።
ኒው ዮርክተ ታይምስ የተባለው የአሜሪካ ጋዜጣ ትናንት ይዞ በወጣው ሰነድ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ የተፈፀሙ አብዛኞች የአየር ድብደባዎች ከወታደራዊ ደህንነት እውቀት ውጪ የተፈፀሙ ናቸው ብሏል።
እንደ ጋዜጣው ሪፖርት በቅርቡ የተሰበሰቡ ተዓማኒነት ያላቸው ሰነዶች እንደሚያመላክቱት የአሜሪካ ጦር በስህተት በጣላቸው ቦምቦች ብቻ ከ1 ሺህ 300 በላይ ንጹሃን ሰዎች እንደተገደሉ ያመላክታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ግልፀኝነትን እና ተጠያቂነትን ከማስፈር አንጻር እስካን በግልጽ የተሰራ ስራ አለመኖሩንም ጋዜጣው አስነብቧል።
በሰነዱ ላይ የአሜሪካ ልዩ ኃይል እንደ አውሮፓውያ አቆጣጠር በሐምሌ ወር 2016 ላይ በሶሪያ የፈፀመው የአየር ድብደባ ለአብነት ተቀምጧል።
በዚህም የአሜሪካ ልዩ ኃይል በሶሪያ የአሸባሪው አይ ኤእ አይ ኤስ የተጠቀምበታል ተብሎ የታመነ ሶስት ስፍራዎች ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ከ120 በላይ አርሶ አደሮች እና የገጠራማ አካባ ነዋሪዎች መገደላቸው ተመላክቷል።
አሜሪካ ባሳለፍነው ነሃሴ ወር ላይም በአፍናጊስታኗ ካቡል ከተማ አሸባሪ ለመምታት ኢላማ አድርጓል ባለችው የአየር ላይ ጥቃት ዘጠኝ የአንድ ቤተሰብ አባላትን መግደሏ ይታወሳል።