አሜሪካ ለሰሜን ኮርያ “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” የእንነጋገር ጥሪ አቀረበች
አሜሪካ የ’እንወያይ ጥሪ’ ብታቀርብም፤ ሰሜን ኮርያ “በአሜሪካ ወላዋይነትና ቅንነት ላይ ጥያቄ አለኝ” ብላለች
ሰሜን ኮርያ በቅረቡ ያደረገቸው የባልስቲክ ሚሳኤል ሙከራ “አሜሪካን ጨምሮ የኮርያ ልሳነ ምድር ስጋት ውስጥ ከቷል
ሰሜን ኮሪያ “አሳሳቢ እና የማይጠቅመውን ” የሚሳይል ሙከራዋን አቁማ ወደ ድርድር መምጣት እንዳባ የአሜሪካ ከፍተኛ በሰሜን ኮርያ ጉዳይ ዲፕሎማት ሰንግ ኪም አሳሰቡ።
ሰንግ ኪም ይህንን ያሉት በሴኡል ከደቡብ ኮርያ ባለስልጠናት ጋር ተገናኝተው እየተካሄደ ባለው የውሃ ውስጥ ባለስቲክ ሚሳኤልን ጨምሮ የሰሜን ኮርያን የወቅቱ የሚሳኤል ሙከራዎች ዙርያ” ከመከሩ በኋላ ነው።
ሙከራዎቹ የመጡት በዋሽንግተን እና በፒዮንግያንግ መካከል በኑክሌር ዲፕሎማሲ ዙርያ ለረዥም ጊዜ በተፈጠረው አለመግባባት እንደሆነ ይገለጻል።
ኪም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ ሰሜን ኮርያ የምታደርጋቸው ትንኮሳዎችን እና የማተራመስ እንቅስቀሴዎችን በመተው ወደ ውይይት እንድትመጣ ጥሪ እናቀርባለን” ብሏል፡፡
ዲፕልማቱ አክልው “ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከሰሜን ኮርያ ጋር ለመወያየት ዝግጁ ነን፤ አሜሪካ ለሰሜን ኮርያ ምንም ዓይነት የጥላቻ ዓላማ እንደሌላትም ግልፅ አድርገናል” ሲሉም ተናግረዋል።
ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ ባካሄደችው የአምስተኛው ዙር የጦር መሣሪያ ሙከራዋ አዲስ የተገነባችውን የባልስቲክ ሚሳኤል ከባህር ሰርጓጅ መርከብ መተኮሷ የሚታወስ ነው።
የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ከባህር ሰርጓጅ መርከብ የተተኮሰው ሚሳኤል በእድገት ላይ ያለ ይመስላል ሲሉ በወቅቱ ተናግረው ነበር።
የሚሳኤል ሙከራው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ከጥር ወዲህ በጣም ከፍተኛ ደረጃን የወሰደ ነው ተብሎለታል።
ከባህር ሰርጓጅ መርከቦች የሚተኮሱ ሚሳኤሎች አስቀድመው ለማወቅ አስቸጋሪና ሰሜን ኮሪያን ሁለተኛ፣ የአፀፋ የማጥቃት ችሎታ እንዲኖራት የሚያስችሉ እንደሆነም ይገለጻል።
የሚሳኤል ሙከራው በጸጥታው ምክርቤት አማካኝነት በሰሜን ኮርያ ላይ የተላለፉ ውሳኔዎች የጣሰ “የሰሜን ኮርያ ጎረቤት ሀገራትንም ሆነ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ የጣለ” ነው ሲሉም ነው ዲፕሎማቱ ኪም የተናገሩት።
ሙከራው “በኮሪያ ልሳነ ምድር ዘላቂ ሰላምና እድገት እንዳይመጣ የሚያደርግና አሳሳቢ ነው”ም ብለዋል።
አሜሪካ እንዲህ ብትልም ፒዮንግያንግ “ዋሽንግተን እና ሴኡል ከራሳቸው ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር በማያያዝ የሚደርጉት ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ተቃበይነት የለውም” ስትል ቆይታለች።
የባህር ሰርጓጅ መርከብ የባላስቲክ ሚሳኤል ሙከራን ተከትሎ አሜሪካ ያሳየችው የተጋነነ ቁጣ “የዋሽንግተን ቅንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው” ስትልም ሰሜን ኮርያ ትወቅሳለች።
የሰሜን ኮርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ “አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ ጋር ምንም ጸብ የለኝም ካለች በኋላ ራስዋ የምታበለጽገውን የምትሞክረውን መሳርያ እኛ ላይ ሲሆን ለወቀሳ መቸኮሏ ወላዋይነቷን ያሳየ እንዲሁም ቅንነቷን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው” ብለዋል።
አሜሪካ “አስከፊ እና ከባድ ውጤት” ሊገጥማት ይችላል ሲሉም የሰሜን ኮርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባ አስጠንቅቀዋል።