የኢራን ዜና አገልግሎት አይአርኤንኤ እንደዘገበው ባለፈው ሰኔ ወር የመጀመሪያውን ባለስቲክ ሚሳይል በሯሷ አቅም ስርታለች
ኢራን እስራኤልን መምታት የሚችል ባለስቲክ ሚሳይል ታጥቃለች?
ኢራን ምዕራባውያንን ባስጨነቀው ፕሮግራሟ የተለያዩ አይነት ሚሳይሎች እና ድሮኖችን እያመረተች ነው።
ሶሪያ ውስጥ በሚገኘው ኢምባሲዋ ላይ ጥቃት ፈጽማለች ያለቻትን እስራኤልን የምታስፈራራው ኢራን ሚሳይሎቿ ወሳኝ ትጥቆቿ ናቸው።
- ባይደን በእስራኤል ላይ “በቅርቡ” ጥቃት ታደርሳለች ያሏትን ኢራን አስጠነቀቁ
- የኢራኑ መሪ ካሚኒ እስራኤል በሶሪያ ላደረሰችው የኢምባሲ ጥቃት "መቀጣት አለባት" አሉ
እንደ አሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ከሆነ ኢራን በቀጣናው ከፍተኛ የባስለስቲክ ሚሳይል ያላት ሀገር ነች።
በከፊል የመንግስት የሆነው አይኤስኤንኤ የተባለው የዜና አገልግሎት እስራኤል ሊደርሱ ይችላሉ ያላቸውን የባለስቲክ ሚሳይል አይነቶችን ዘርዝሯል።
ዝርዘሩ 17ኪሎሜትር በሰአት የሚጓዘውን እና እስከ 2500 ኪሎሜትር ድረስ የመወንጨፍ አቅም ያለውን 'ሰጂል'ን፣ 2000 ኪሎሜትር ድረስ መወንጨፍ የሚችለውን 'ኬይባር'ን እና በአሜሪካ ጥቃት በተገደለው የኩድስ ፎርስ ኮማንደር ቃሲም ሱሌማኒ ስም የተሰየመውን እና እስከ 1400ኪሎሜትር የሚወነጨፈውን ሚሳይል ያካትታል።
ዋነኛ የድሮን አምራች የሆነችው ኢራን ባለፈው ነሀሴ ወር 300ኪሎግራም ክብደት ያለው ተተኳሽ ይዞ እስከ 2000 ኪሎሜትር ድረስ የሚበር ሞሀጀር-10 የተባለ ዘመናዊ ድሮን መስራቷን ገልጻለች።
የኢራን ዜና አገልግሎት አይአርኤንኤ እንደዘገበው ባለፈው ሰኔ ወር የመጀመሪያውን ባለስቲክ ሚሳይል በሯሷ አቅም ስርታለች።
ሀይፐርሶኒክ ሚሳይሎች ከድምጽ ፍጥነት በአምስት እጥፍ የመጓዝ ፍጥነት ያላቸው በመሆኑ መትቶ ለጣል አስቸጋሪ የሚባሉ ናቸው።
አሜሪካ እና አውሮፓውያን ቢቃወሙም፣ ኢራን የሚሳይል ፕሮግራሟን እንደምትገፋበት ነው የገለጸችው።
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ማህበር እንደገለፈው የኢራን ሚሳይል ፕሮግራም የሩሲያን እና የሰሜን ኮሪያን ዲዛይን መነሻ ያደረገ ነው ብሏል።
ማህበሩ እንደገለጸው ከኢራን የረጀም እና የመካከለኛ ርቀት ባለስቲክ ሚሳይሎች መካከል 300ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል ሸሀብ-1፣700 ኪሎሜተር መወንጨፍ የሚችል ዞልፋጋር፣ 800 ኪሎሜትር መወንጨፍ የሚችል ሸሀብ-3 በግምባታ ላይ ያሉት 2000ኪሎሜትር መወንጨፍ የሚችለው ኢሜድ-1 እና እስከ 2500 ኪሎሜትር መጓዝ የሚችለው ሰጂል ይገኙበታል።
ኢራን እንደ ኬኤች-55 አይነት ያሉ 3000 ኪሎሜትር የሚወነጨፍ ኑክሌር ተሸካሚ ክሩዝ ሚሳይልም ታጥቃለች።