ፈረንሳይ ኢራን ያሰማችውን ዛቻ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ 4 ሀገራት እንዳይሄዱ አስጠነቀቀች
የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ባለፈው ረብዕ እስራኤል "መቀጣት አለባት" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈረንሳያውያን ወደ ኢራን፣ ሊባኖስ፣ እስራኤል እና ፍልስጤም እንዳይሄዱ በዛሬው እለት መክሯል
ፈረንሳይ ኢራን ያሰማችውን ዛቻ ተከትሎ ዜጎቿ ወደ 4 ሀገራት እንዳይሄዱ አስጠነቀቀች።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፈረንሳያውያን ወደ ኢራን፣ ሊባኖስ፣ እስራኤል እና ፍልስጤም እንዳይሄዱ በዛሬው እለት መክሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኤክስ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ መቀመጫቸውን ኢራን ያደረጉ ዲፕሎማቶች ወደ ፈረንሳይ እንደሚመለሱ እና የፈረንሳይ ሰራተኞች በኢራን፣በሊባኖስ፣ በእስራኤል እና በፍልስጤም ግዛቶች እንዳይሰሩ ይደረጋል ብሏል።
የኢራኑ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ባለፈው ረብዕ እስራኤል በደማስቆ በሚገኘው የኢራን ኢምባሲ ላይ አድርሳዋለች ላሉት ጥቃት "መቀጣት አለባት" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
ካሚኒ ይህን ዛቻ ያሰሙት እስራኤል ሳታደርሰው አትቀርም በተባለው የሚያዝያ አንዱ ጥቃት ሰባት ወታደራዊ አማካሪዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
የኢምባሲው ጥቃት በባላንጣዎቹ እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ውጥረት ከፍ አድርጎታል ተብሏል።
ካሚኒ "ሰይጣናዊው መንግስት ስህተት ስርቷል፤ መቀጣት አለበት። ይቀጣልም" ሲሉ ነበር የዛቱት።
እስራኤል ፈጽመዋለች በተባለው በዚህ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሁለት የኢራን ጀነራሎች እንደሚገኙበት ኢራን ማስታወቋ ይታወሳል።
የኢራንን ዛቻ የሰማችው እስራኤል ከኢራን ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም አይነት ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆኗን እየገለጸች ነው።