የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር መግዣን 101 ብር ያደረሰ ሲሆን፤ በ111 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከካሳለፍነው ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 50 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 3 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት በንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.1287 ብር እየተገዛ በ116.6242 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.2889 ብር እየተገዛ በ114.6507ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ103.4984 ብር እየተገዛ በ115.9182 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.0057 ብር እየተገዛ በ117.1666 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የዶላር መግዣ ዋጋን ለመጀመሪያ ጊዝ ከ100 ብር ያሳለፈ ሲሆን፤ ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.0041 ብር እየገዛ በ111.1045 ብር እየሸጠ ነው።