የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ95 ዶላር እገዛ፤ በ101 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 45 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የሀምሌ 30 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት በወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.6434 ብር እየተገዛ በ113.8406 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.9253 ብር እየተገዛ በ112.0271 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኦሮሚያ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.8546 ብር እየተገዛ በ113.9657 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
በንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.6391 ብር እየተገዛ በ106.7437 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
አዋሽ ባንክ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.1531 ብር እየተገዛ በ111.1699 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ95.6931 ብር እየገዛ በ101.4347 ብር እየሸጠ ነው።