የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ95 ብር እገዛ፤ በ101 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከካሳለፍነው ጀምሮ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 50 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የነሃሴ 2 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት በኦሮሚያ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.0047 ብር እየተገዛ በ117.1655 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
በወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.6434 ብር እየተገዛ በ113.8406 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.9263 ብር እየተገዛ በ112.0282 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በንብ ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.0959 ብር እየተገዛ በ113.3274 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ95.6931 ብር እየገዛ በ101.4347 ብር እየሸጠ ነው።