ኢኮኖሚ
የነሃሴ 1 የባንኮች ውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች 10ኛ ቀኗን ይዛለች
የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ተመኑ ባለፉት ቀናት የተወሰነ መረጋጋት አሳይቷል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረች 10ኛ ቀኗን ይዛለች።
ባንኮችም በየእለቱ አዲስ የምንዛሬ ዋጋ ማውጣታቸውን ቀጥለዋል።
ዳሽን ባንክ ዛሬ ነሃሴ 1 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ አንድ ዶላር በ100.99 ብር እየገዛ በ112.10 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ወጋገን ባንክ ይፋ ባደረገው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አንድ ዶላር በ101.64 ብር ገዝቶ በ113.84 ብር እየሸጠ መሆኑን አመላክቷል።
ንብ ባንክም የዶላር መግዣ ዋጋን 101.09 ብር አድርሷል። ባንኩ አንድ የእንግሊዝ ፓውንድ በ126.35 ብር እየገዛ በ144.87 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ በዶላር መግዣና መሸጫ ዋጋ ላይ ከአምስት ቀናት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ 1 ዶላር በ95.69 ብር እየገዛ በ101.43 ብር በመሸጥ ላይ ነው።
ኦሮሚያ ባንክም የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አስቀጥሎ አንድ ዶላር በ100.85 ብር እየገዛ በ113.96 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ አድርጓል።