ዶላር በባንኮች በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች የህዳር 23 የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ሲያደርጉ ተቀራራቢ የዶላር መግዣ ዋጋን አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክም ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ ከሁለት ቀን በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6420 ብር ገዝቶ በ127.1348 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ የህዳር 23 ቀን 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6189 ብር ገዝቶ በ127.1113 ብር እየሸጠ መሆኑን ጠቁሟል።