የጣሊያኗ መንደር በትራምፕ ምርጫ ማሸነፍ ድብርት ውስጥ ለገቡ አሜሪካውያን በአንድ ዩሮ የቤት ሽያጭ ማቅረቧ ተገለጸ
በሳርዲና ደሴት ላይ የምትገኘው ኦሎላይ መንደር እየተመናመነ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመጨመር ያዘመሙ ቤቶችን "በአንድ ስፒሪስ" ዋጋ ለሽያጭ አቅርባለች

ኦሎላይ በ2018ም በተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለሽያጭ አቅርባ ነበር
በሳርዲና ደሴት ላይ የምትገኘው ኦሎላይ መንደር እየተመናመነ የመጣውን የህዝብ ቁጥር ለመጨመር ያዘመሙ ቤቶችን "በአንድ ስፒሪስ" ዋጋ ለሽያጭ አቅርባለች።
መንደሯ አሜሪካውያንን ለመሳብ በከፈተችው ጽረ ገጽ "አለም አቀፋዊው ፖለቲካ ደብሯችኋል? አዲስ እድሎች እና ሚዛናዊ ህይወት ይፈልጋሉ" የሚል ጥያቄ አቅርባለች።
"በማራኪዋ ሳርዲና ህይወት ለመጀመር ጊዜው አሁን ነው። መንደሯ በገጠሯ ሳርዲና ማዕከል የምትገኝ ሲሆን ታዋቂ የባህር ዳርቻዎቿ ለአንድ ሰአት ያህል ከተጓዙ በኋላ የሚገኙ ናቸው።
የኦሎላይ ባለስልጣናት ከአንድ ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች የመምረጥ ስራው መጠናቀቁን እና "ብዙ ገዥዎች" እነዚህን ንብረቶች በተሳካ ሁኔታ ማደሳቸውን ተናግረዋል። ባለስልጣናቱ አክለውም እንደገለጹት ማደስ የማይፈለጉ አሜሪካውያን ያለቀለት ቤት እስከ 100ሺ ዩሮ መግዛት ይችላሉ።
መንደሯ የውጭ ዜጎች በቀላሉ እንዲቋቋሙ ገንቢዎችን እንደምታገናኛቸው እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እንደምታደርግ ቃል ገብታለች።
ምንም እንኳን የመንደሯ ባለስጣናት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ቢገልጹም፣ ምስሉ ስላልወጣ የአንድ ዶላር ዋጋ ያለው ቤት በምን ሁኔታ እንደሚገኝ አይታወቅም።
የመንደሯ ከንቲባ ፍራንሲስኮ ኮሉምቡ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት ቦታው የተቋቋመው የዶናልድ ትራምፕ ማሸነፍ የተወሰኑ አሜሪካዊያን እንዲጨነቁ ካደረገ በኋላ ነው።
"በእውነት እንፈልጋችኋለን፤ ከሁሉም በላይ አሜሪካውያን ላይ ትኩረት አድርገናል"ብለዋል ከንቲባው።
"በርግጥ የሌላ ሀገር ሰዎች ቢያመለክቱም አንከለክልም፤ ነገርግን አሜሪካውያን ፈጣን አገልግሎት ያገኛሉ። መንደሯ እንደታንሰራራ ያደርጓታል ብለን በእነሱ እንተማመናለን።"
ኮለምቡ እንዳሉት እስካሁን 40ሺ ሰዎች መረጃ ጠይቀዋል።
ኦሎላይ እንዲህ አይነት ጥሪ ስታቀርብ የመጀመሪያዋ አይደለም፤ በ2018ም በተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለሽያጭ አቅርባ ነበር። መንደሯ ይህን የምታደርገው ከ2250 ወደ 1300 የቀነሰውን የህዝብ ቁጥር ወደ ነበረበረበት ለመመለስ ተስፋ በማድረግ ነው።