ፕሬዝደንት ፑቲን ለወታደራዊ ዘርፍ ትኩረት ያደረገውን የ2025-2027 በጀት አጸደቁ
የሀገሪቱ የቀጣይ አመት በጀት የ25 በመቶ ወታደራዊ ወጭ ጭማሪን የሚያካትት ሲሆን ከሶቬት መፈራረስ በኋላ በከፍተኛ ሚስጥር የሚያዝ ነው

ሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረባቸው የንግግር ቅድመ ሁኔታዎች የተራራቁ በመሆናቸው ምክንያት ጦርነቱን ለማስቆም የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም
ፕሬዝደንት ፑቲን ለወታደራዊ ዘርፍ ትኩረት ያደረገውን የ2025-2027 በጀት አጸደቁ።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በወታደራዊ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረገ ወታደራዊ በጀት ማጽደቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሀገሪቱ የቀጣይ አመት በጀት የ25 በመቶ ወታደራዊ ወጭ ጭማሪን የሚያካትት ሲሆን ከሶቬት መፈራረስ በኋላ በከፍተኛ ሚስጥር የሚያዝ ነው።
ከማህበራዊ ጉዳዮች እና የቴክኖሎጂ ልማት ጎን ለጎን በዩክሬን እየተካሄደ ያለው "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" የበጀት ቅድሚያ እንደሚያስፈልገው ሞስኮ አምናለች።
የሩሲያ መንግስት ረቂቅ በጀቱን "ሚዛኑን የጠበቀ" መሆኑን እና የበጀት ክፍተቱ በዚህ አመት ከተገመተው 1.7 በመቶ ወጀ 0.5 በመቶ ዝቅ ማለቱን አቅርቧል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ መፍቀዳቸው እና ይህን ተከትሎ ሩሲያ ኦርሽኒክ የተባለ የመካከለኛ ርቀት ሚሳይል ወደ ዩክሬን ማስወንጨፏ ጦርነት ጡዘት ላይ ደርሷል።
ምዕራባውያን ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሊያስታጥቁ ይችላሉ የሚሉ ዘገባም በቅርቡ ወጥቶ ነበር። ፑቲን ዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ የምትታጠቅ ከሆነ ሩሲያ በኑክሌር ጦር መሳሪያ መልስ ከመስጠት ውጭ አማራጭ እንደማይኖራት አስጠንቅቀዋል።
ሩሲያ እና ዩክሬን ያቀረባቸው የንግግር ቅድመ ሁኔታዎች የተራራቁ በመሆናቸው ምክንያት ጦርነቱን ለማስቆም የተደረጉ ጥረቶች አልተሳኩም።
ዩክሬን የሩሲያን ጦር ከግዛቷ መውጣትን በቅደመ ሁኔታነት ስታስቀምጥ፣ ሩሲያ ደግሞ ጦርነቱ የሚቆመው በከፊል የያዘቻቸውን ዩክሬን ግዛቶች ይዛ ስትቆይ መሆኑን ገልጻለች።