በታህሳስ 18 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ዶላር ከ124 ብር ጀምሮ እየገዙ እስከ 127 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛሉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላርን በ123 ብር ገዝቶ በ126 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ የታህሳስ 18 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ለአንድ ዶላር 124.7045 ብር መግዣ፤ 127.1986 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርቧል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8066 ብር ገዝቶ በ127.3027 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክ የታህሳስ 18 2017 የውጭ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.8474 ብር ገዝቶ በ127.3444 ብር እየሸጠ ነው።
ኦሮሚያ ባንክ ከ28 ቀናት በፊት ያወጣውን የዶላር መግዣ ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።