ሩሲያ የዩክሬን ደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣናቷን ለመግደል ያደረገውን ሴራ አከሸፍኩ አለች
"ሩሲያ በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ሊፈጸሙ የነበሩ ተከታታይ የግድያ ሙከራዎችን ተከላክላለች" ሲል የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት ገልጿል

ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ደህንነት የሩሲያን የኑክሌር ኃይል መከላከያ ኃላፊን ሞስኮ ከሚገኘው መኖሪያቸው በሚወጡበት ወቅት ሞተር ሳይክል ላይ ቦምብ በማጥመድ ገድሏል
የሩሲያ ፌደራል ሴኩሪቲ ሰርቪስ(ኤፍኤስቢ) የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ የሩሲያ ባለስልጣናትን እና ቤተሰቦቻቸውን በሞስኮ ለመግደል ያደረገውን ሙከራ ማክሸፉን በዛሬው እለት ገልጿል።
ባለፈው ሳምንት የዩክሬን ደህንነት የሩሲያ የኑክሌር፣ የባዮሎጂካል እና የኬሚካል መከላከያ ኃይል ኃላፊ የሆኑትን ሌትናንት ጀነራል ክሪሎቭን ሞስኮ ከሚገኘው መኖሪያቸው በሚወጡበት ወቅት ሞተር ሳይክል ላይ ቦምብ በማጥመድ ገድሏል።
ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ከጥቃቱ ጀርባ የዩክሬን ደህንነት አለበት።
ከየካቲት 2022 ጀምሮ በዩክሬን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ያለችው ሩሲያ ጥቃቱን በዩክሬን የተፈጸመው የሽብር ተግባር ነው ስትል ገልጻዋለች።
"ሩሲያ በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ሊፈጸሙ የነበሩ ተከታታይ የግድያ ሙከራዎችን ተከላክላለች" ሲል የሩሲያ ፌደራል ደህንነት አገልግሎት ገልጿል።
አገልግሎቱ በመግለጫው "እነዚህን ጥቃቶች በማዘጋጀት የተሳተፉ አራት ሩሲያውያን ታስረዋል" ብሏል።
በሶቭየት ህብረት ጊዜ የነበረውን የደህንነት ተቋም የተካው ኤፍኤስቢ የሩሲያ ዜጎች በዩክሬን መመልመላቸውን ጠቅሷል። ኤፍኤስቢ አንዱ ተጠርጣሪ ጥቃት ከሶስት ቀናት በፊት ቦምብ ይዞ መገኘቱን ከመግለጽ ውጭ ጥቃቱ ለመቼ ታስቦ እንደነበር ግልጽ አላደረገም። የሩሲያ መንግስት ቴሌቪዥን በዩክሬን ደህንነት ተመልምለዋል ያላቸውን ሩሲያውያን ምስል አሳይቷል።
ሞስኮ ዩክሬን የስነልቦና ጉዳት ለማድረስ በማስብ በሩሲያ መሬት ላይ ተከታታይ የግድያ ሙከራ እያደረገች ነው ስትል ከሳታለች። በሩሲያ ታዋቂ የሆነው ፖለቲከኛ ልጅ ዳርያ ዱጊና በሐምሌ 2022 በሞስኮ መገደሏ ይታወሳል። ለዚህ ግድያ ዩክሬን እጇ ሳይኖርበት አይቀርም የሚል ግምት አለ።
ሶስት አመታት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ሲቀጥል፣ ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን ግስጋሴ እያደረገች ትገኛለች።