የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበኩሉ አንድ ዶላር በ121 ብር ገዝቶ 123 ብር እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ የአንድ ብር ጭማሪ አድርጎ ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ123.8506 ብር እየገዛ በ126.3276 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አቢሲኒያ ባንክ ከትናንቱ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላርን በ122.8540 ብር እየገዛ በ125.3131 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.8512 ብር እየገዛ በ125.3082 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበኩሉ አንድ የአሜሪካ ዶላርን 121.2433 ብር እየገዛ 123.6682 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ አስታውቋል።