በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አዲስ ውጥረት ማገርሸቱን ተከትሎ ምን አዳዲስ ነገሮች ተከስተዋል?
ዩክሬን ከአሜሪካ ሚሳዔሎች በተጨማሪ የብሪታያ ክሩዝ ሚሳዔሎችንዳ ወደ ሩሲያ ተኩሳለች
የሩሲያ የአጸፋ ምት ፍራቻ በርካታ ምእራባውያ ኤምባሲያቸውን እየዘጉ ሲሆን፤ ኪቭ ስጋት ውስጥ አድራለች
ዩክሬን የምእራባውያን ሚሳዔሎችን ወደ ሩሲያ ግዛቶች መተኮስ መጀመሯን ተከትሎ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወደ አዲስ ውጥረት ተሸጋግሯል።
ዩክሬን ከምእራባውያ ሀገራት ፈቃድ ማግኘቷን ተከትሎ የሩሲያ ግዛቶችን በሚሳዔል መምታቷን የተቀጠለች ሲሆን፤ አዳሩን ደግሞ የብሪታያ ሚሳዔሎችን ወደ ሩሲያ ግዛት ተኩሳለች።
ከጦር አውሮፕላን ላይ የሚተኮሱት የብሪታኒያ ስቶርም ሻደው ክሩዝ ሚሳዔሎች እያዳንዳቸው 1 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ ሲሆን፤ እስከ 250 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የሚገኝ ኢላማን መምታት የሚችሉ ናቸው።
ዩክሬን አዳሩን 12 “ስቶርም ሻደው” የተባሉ የብሪታያ ክሩዝ ሚሳዔሎችን ወደ ሩሲያዋ ኩርስክ ክልል መተኮሷን የሩሲያ መንግስት ደጋፊ የቴሌግራም ገጾች ጽፈዋል።
የዩክሬን ጦር በጉዳዩ ላይ በሰጠው ማብራያ፤ በብሪታያ “ስቶርም ሻደው” ክሩዝ ሚሳዔሎችን በመጠቀም ከዩክሬን ድንብር በ168 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የሩሲያዋ ቤልግሮድ ክልል ጉብኪን ከተማ ውስጥ የሚገኝ የሩሲያ ኮማንድ ፖስት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።
በመሬት ላይ እየተካሄደ ባለው ውጊያ ደግሞ የሩሲያ ጦር ግስጋሴውን የቀጠለ ሲሆን፤ በምስራቅ ዩክሬን ዶኔስክ ክልል ውስጥ የሚገኝ መንደር መቆጣጠሩን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ሩሲያ በምእራባውያ መሳሪያዎች ጥቃት ከተፈጸመባት በኋላ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ሊፈጸም ነው በሚል በዩክሬን ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጥቃት መፈጸሟን የኪቭ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ሩሲያ መረጃውከዩክሬን የወጣ በማስመሰል እና ሊደርስ ስለሚችለው ግዙፍ የአየር ጥቃት የውሸት ማስጠንቀቂያ በማሰራጨት “ትልቅ የመረጃ-ስነ-ልቦናዊ ጥቃት” አድር ሳለች ሲሉ የኪየቭ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ሩሲያ ከተፈጸመባት የሚሳዔል ጥቃት በኋላ ልትወስደው የምትችለውን የአጸፋ እርምጃ በመፍራት አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያን ሀገራት በኪቭ የሚገኝ ኤምባሲዎቻውን በመዝጋት ላይ ይገኛሉ።
የሩሲያ የውጭ የደህንነት አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ሰርጌይ ናሪሽኪን፤ የክሬን የሩሲያን ድንበር ጥሳ ጥት እንደትፈጽም የረዱ እያንዳንዱ የኔቶ አባ ሀገራትን ትቀጣለች ሲሉ ዝተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ዩክሬን በረጅም ርቀት ሚሳዔል ሩሲያን የማጥቃት ድርጊት ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጀመሩት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ተመጣጣኝ ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንቱ ቭላድሚር ፑቲን ባሳለፍነው ማክሰኞ የተሻሻለውንና የሩሲያን የኒዩክሌር መሳሪያ አጠቃቀም የሚወስነው ህግ ማጽደቃቸውን ክሬምሊን አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ዋሽንግተን የኒዩክሌር ጦርነት ከሚያስነሳ ተግባሯ እንድትታቀብ ማሳሰባቸውን ክሬምሊን ጠቁሟል።
ሩሲያ በ2020 በይፋ ያወጣችውን የኒዩክሌር ህግ ማሻሻሏን ስትገልጽ የቆየች ሲሆን፥ ባይደን ለኬቭ ይሁንታ በሰጡ ማግስት ነው ፑቲን ማሻሻያውን ያፀደቁት።
ማሻሻያው ኒዩክሌር ያልታጠቁ ሀገራት ከታጠቁት ጋር በመተባበር በሩሲያ ላይ ጥቃት ካደረሱ በሞስኮ ላይ “የጋራ ጥቃት” እንደከፈቱ ይቆጠራል የሚል ሃሳብ አካቷል።
ሩሲያ የኒዩክሌር መሳሪያዎቿን መቼ መጠቀም እንዳለባት በግልጽ የሰፈረበት ህግ፥ ድንበር አቋራጭ የሚሳኤል፣ የአየር እና ድሮን ጥቃት ከተፈጸመባት አውዳሚዎቹን መሳሪያዎች መጠቀም እንደምትጀምር የሚፈቅድ ነው።