በጥቅምት 28 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ ዶላርን በ121 ብር ገዝቶ በ123 ብር እየሸጠ ነው
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ118 እስከ 121 ብር የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 28 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ማሻሻያ ባያደርገውም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ጎህ ቤቶች ባንክ ከኦሮሚያ ባንክ በመቀጠል ከፍተኛ የዶላር መግዣ ዋጋ ያቀረበ ባንክ ነው። ባንኩ አንድ ዶላር በ121.2716 ብር ገዝቶ በ123.6970 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.0859 ብር ገዝቶ በ123.5076 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የጥቅምት 28 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.4570 ብር እየገዛ በ122.8661 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።