የ2024 ቱን የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ትራምፕ ማን ናቸው?
ትራምፕ የአሜሪካን እየተፈራረቁ የሚመሩት ሁለት ግዙፍ ፓርቲዎች ማለትም የሪፐብሊካን እና የዲሞክራት ፓርቲዎች አባል ሆነው ያውቃሉ
ትራምፕ በዘንድሮው ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ሀሪስን በ277 የውኪል ድምጽ በማሸነፍ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝደንት መሆናቸው ተረጋግጧል
የ2024 ቱን የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ትራምፕ ማን ናቸው?
ዶናልድ ትራምፕ የተወለዱት ከ78 አመታት በፊት በአሜሪካ ነው ዮርክ ከተማ ነው።
ትራምፕ የአሁኗ ባለብቤታቸውን ሜላኒያ ትራምፕን ጨምሮ ከ1977 ጀምሮ ሶስት ሚስቶችን አግብተዋል።
በአሜሪካ አንጋፋ ፖለቲከኛ መሆን የቻሉት ትራምፕ በዋናነት ሪልኢስቴት እና ሀቴል ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብት ናቸው።
ትራምፕ የአሜሪካን እየተፈራረቁ የሚመሩት ሁለት ግዙፍ ፓርቲዎች ማለትም የሪፐብሊካን እና የዲሞክራት ፓርቲዎች አባል ሆነው ያውቃሉ። በ1987 የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል ሆነው የተዘመዘገቡት ትራምፕ 1999 የሪፎርም ፓርቲ፣ በ2001 የዲሞክራት ፓርቲ አባል ሆነው ተመዝገበው ነበር።
ትራምፕ በ2009 እንደገና የሪፐብሊካን አባል፣ በ2012 ደግሞ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ሆነው ቀርበው ነበር።
በ2000 ትራምፕ በአሜሪካ በትልቅነቱ ሶስተኛ የሆነውን ሪፎርም ፓርቲን በመወከል ለሶሰት ወራት በምርጫ ቅስቀሳ የተሳተፉ ሲሆን ብዙም ሳይቆዩ ከውድድሩ ወጥተዋል።
ትራምፕ በ2012ቱ ምርጫ እጩ በመሆን ከቀረቡት ጥቁር አሜሪካዊ ባራክ ኦባማ ጋር ይወዳደራሉ ተብሎ የተወራ ቢሆንም ትራምፕ እንደማይወዳደሩ አሳወቁ።
የትራምፕ የፕሬዝደንትነት ህልም ከቁምነገር አይቆጠርም ነበር።
ትራምፕ በሐምሌ 2015 በ2016ቱ የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ ይፋ አደረጉ።
የትራምፕ የምርጫው ቅስቀሳ መጀመሪያ ላይ በፖለቲካ ተንታኞች ዘንድ ትከረት አልተሰጠውም ነበር፤ ነገርግን ቀስ እያለ ከፍተኛ ተቀባይነት ሊያገኝ ችሏል።
ትራምፕ የዲሞክራቷን እጩ ሂላሪ ክሊንተንን አሸንፈው ኃይት ሀውስ በመግባት አሜሪካን ከ2017-2021 መርተዋል።
'ፖፑሊስት' ተደርገው የሚወሰዱት ትራምፕ ጠንከራ የጸረ-ስደተኞች ፖሊሲን በማቀንቀን ይታወቃሉ።
አራት አመት አሜሪካን የመሩት ትራምፕ በ2020 በተካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ በጆ ባይደን ተሸንፈዋል። ነገርግን ትራምፕ ሸንፈታቸውን አምነው አልተቀበሉም።
ምንም እንኳን ፍርድ ቤቶች፣ የግዛት መንግስታት እና የራሳቸው የቀድሞ አስተዳደር አባላት አሸንፌያለሁ ማለታቸውን ውድቅ ቢያደርጉባቸውም፣ ትራምፕ በ2020 ምርጫ የተሸነፉት ድምጽ ተሰርቀው እንደሆነ ያምናሉ።
ትራምፕ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ የመንግስት ሚስጥርን በማሸሽ፣ በታክስ ማጭበርበር፣ በጾታዊ ጥቃት ጨምሮ በበርካታ ወንጀሎች ተከሰው ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ቆይተዋል።
ትራምፕ በዘንድሮው ምርጫ 2024 ተቀናቃኛቸውን ከማላ ሀሪስን በ277 የውኪል ድምጽ ወይም 'ኢሌክቶራል ቮት' በማሸነፍ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝደንት መሆናቸው ተረጋግጧል።