የ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል
በአሜሪካ ምርጫ የአሸናፊ እና ተሸናፊ ደጋፊዎች ስሜት በፎቶ የ2024ቱ የአሜሪካ ምርጫ በዶናልድ ትራምፕ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በርካታ ድራማዊ ክስተቶችን ባስተናደው የዘንድሮው ምራጫ ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ቢሆንም የሪፐብሊካኑ ዕጩ ዶናልድ ትራምፕ ከ2020 ምርጫ በኋላ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት የሚያስገባቸውን ድምጽ አግኝተዋል፡፡
ከትራምፕ ጋር ባደረጉት የምርጫ ክርክር በወሰዱት ብልጫ በዘንድሮው ምርጫ ያሸናፊነት ግምት ያገኙት ካማላ ሃሪስ የማሸነፍ እድላቸው ተሟጧል፡፡
በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት በሴቶች እና በጥቁሮች የተሻለ ድጋፍ እንዳገኙ ሲነገርላቸው የነበሩት ሀሪስ የመጀመርያዋ ሴት ፕሬዝዳንት የመሆን እድላቸው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ምርጫው በይፋ ከተከፈተ አንስቶ ትራምፕ የምርጫውን ውጤት በሚወስኑት ግዛቶች ከፍተኛ ድምጽ በማግኝት መምራታቸውን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው አሸነፊነታቸውን በማወጅ ደስታቸውን መግለጽ የጀመሩት ቀደም ብሎ ነበር፡፡
የዴሞክራት እና የሀሪስ ደጋፊዎች በበኩላቸው በምርጫው ውጤት መከፋታቸው እና ማዘናቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ካማላ ሀሪስም ምሽት ላይ ሊያደርጉት የነበረውን የምርጫ ምሽት ድግስ በመሰረዝ ሲጠባበቋቸው የነበሩ ደጋፊዎች እንዲበተኑ አድርገዋል፡፡