ተጠባባቂ የእስራኤል ወታደሮች በጦርነቱ ምክንት ኢኮኖሚያቸው እየደቀቀ ነው በሚል የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ጠይቀዋል
እስራኤል አዲስ ወታደር ለመመልመል ፈተና እንደገጠማት ተገለጸ፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ልተጠበቀ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በሊባኖሱ ሂዝቦላህ እና እስራኤል ጦር መካከል ይፋዊ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን የእስራኤል ጦር ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ ገብቶ ከሂዝቦላህ ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል፡፡
እስካሁን ባሉት ጊዜ ውስጥ እስራኤል 300 ተጠባባቂ ጦሯን የጠራች ሲሆን በጋዛ እና በሊባኖስ በተደረጉ ውጊዎች 367 ወታደሮቿ ተገድለውባታል፡፡
በሊባኖስ ተጨማሪ የውጊያ ግንባር ለመክፈት አቅዳለች የተባለችው እስራኤል የወታደር እጥረት እንደገጠማት ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በእስራኤል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ዜጎች ብሔራዊ ጦሩን ተቀላቅለው የማገልገል ግዴታ አለባቸው፡፡
ይህን ተከትሎ ጦሩን እንዲቀላቀሉ ጥሪ የቀረበላቸው እስራኤላዊን በጦርነቱ ተሰላችተዋል የተባለ ሲሆን የመዋጋት ፍላጎታቸውም ቀንሷል ተብሏል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በተጀመረው የሊባኖስ ውጊያ ብቻ 37 የእስራኤል ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን በጋዛ ለአንድ ዓመት ከቆየው ጋር ሲነጻጸር ጉዳቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ ምክንያት በእስራኤል የንግድ እንቅስቃሴዎች እክል መግጠሙን ተከትሎ በተጠባባቂ ጦር የተያዙ እስራኤላዊን ወደ ውጊያ ግንባር የመጓዝ ያላቸው ፍጎት ቀንሷልም ተብሏል፡፡
ብሔራዊ ግዳጃቸውን ለመፈጸም ጦሩን የሚቀላቀሉ እስራኤላዊያን ዜጎች ስራቸውን የማጣት፣ ቤተሰባቸውን ለአደጋ የማጋለጥ እና ሌሎች ጉዳቶችን ደርሳል በሚል ለመቀላቀል ፍላጎት እያጡ አንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አልትራ ኦርቶዶክስ የሚባሉት እስራኤላዊያን ፈጣሪን የሚፈሩ ማህበረሰቦች ናቸው በሚል ጦሩን እንዳይቀላቀሉ በሚል ህጋዊ ምህረት መደረጉ የሀገሪቱ ጦር የሰው ሀይል እጥረት እንዲያጋጥመው ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡