በታህሳስ 7 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች አንድ የአሜሪካ ዶላርን እስከ 124 ብር ገዝተው እስከ 127 ብር በመሸጥ ላይ ናቸው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ23 ቀናት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ23 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ የታህሳስ 7 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከ13 ቀናት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር እየገዛ በ127.3679 ብር እየሸጠ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6477 ብር ገዝቶ በ127.1407 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
አቢሲኒያ ባንክ ከሶስት ቀናት በፊት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ124.5400 ብር እየገዛ በ127.0308 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ጸደይ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላር በ124.7368 ብር ገዝቶ በ127.2316 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።