እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው ድብደባ ከ50 ላይ ፍሊስጤማውያን መሞታቸው ተገላጸ
በድብደባው ከሞቱት ውስጥ ጋዜጠኞች፣ የጤና ባለሙያዎችና የነፍስ አድን ሰራተኞች ይገኙበታል
እስራኤል “ድብደባው ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ የነበሩ ሚሊሻዎች ኢላማ ያደረገ ነው” ብላለች
እስራኤል በጋዛ በአየር እና በምድር በተፈጸቻቸው ድብደባዎች ቢያንስ የ53 ፍሊስጤማውያን ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
በአየር ድብደባው ከሞቱት መካከል ጋዜጠኖች፣ የህክምና ባለሙያዎች እና የነፍስ አድ ሰራተኞች እንደሚገኙበትም ሮይተርስ ዘግቧል።
እስራኤል የአየር ድብደባ ከፈጸመችባቸው ቦታዎች መካከል ኑስሪያት የገበያ ስፍራ አንዱ ሲሆን፤ የአል ጀዚራ ጋዜጠኛ አህመድ አል ሎውህ፣ አንድ የጤና ባለሙያ እና ሌሎች አምስት ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።
በኑስሪያት የስደተኞች ካምፕ ላይ በተፈጸመ ሌላኛው የእስራኤል ጥቃት ደግሞ ህጻናትን ጨምሮ አምስት ሰዎች መገደላቸው ነው የተገለጸው።
የእስራኤል ጦር “ድብደባው ጥቃት ለመፈጸም በዝግጅት ላይ የነበሩ ሚሊሻዎች ኢላማ ያደረገ ነው” ያለች ሲሆን፤ የተገደለው ጋዜጠኛም ከእነሱ ጋር ሲሰራ የነበረ ነው ብላለች።
አል ጀዚራ በጋዜጠኛው ላይ የተፈጸመው ግድያ ያወገዘ ሲሆን፤ እስራኤል ጋዜጠኛው የታጣቂዎች አባል ነበር በሚል ባቀረበችው ውንጀላ ላይ ግን አስተያየት አልሰጠም።
እስራኤል በደቡባዊ ካን ዩኒስ በሚገኘው በተመድ በሚተዳረው እና ተፈናቃዮች በተጠለሉበት አህመድ ቢን አብዱላዚዝ ትህር ቤት ላይ በፈጸመአችው የአየር ድብደባም 20 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።
በሰሜናዊ ቤይ በሚገኝ ተምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ሌላ ጥቃትም 43 ፍሊስጤማውያን መሞታቸውም ተነግሯል።