ሲፈለግ የነበረን መጽሀፍ ከ 50 አመታት በኋላ ወደ ቤተ መጽሃፍ የመለሰው ግለሰብ
በአሜሪካ በዴትሮይት ዳርቻ ያደገው ግለሰብ ከ 50 አመታት በኋላ የተዋሰውን የቤዝቦል መጽሀፍ በልጅነት ጊዜው ይጠቀምበት ለነበረው ቤተመጽሃፍ መልሷል
የ63 አመቱ የቺካጎ ነዋሪ ቸክ ሂልደብራድት ለምስጋና ቀን በዋረን የሚገኘውን የህዝብ ቤተመጽሃፍ በጎበኘበት ወቅት ነበር መጽሃፉን የተዋሰው
አሜሪካ በዴትሮይት ዳርቻ ያደገው ግለሰብ ከ 50 አመታት በኋላ የተዋሰውን የቤዝቦል መጽሀፍ በልጅነት ጊዜው ይጠቀምበት ለነበረው ቤተመጽሃፍ መልሷል።
ግለሰቡ ለምን መጽሀፉን እንዳቆየው ሲጠየቅ "ማስቀመጥ ትችላለህ፣ ግን ጥሩ አይደለም" የሚል ምላሽ መስጠቱን ኤፒ ዘግቧል።
የቺካጎው የ63 አመት ነዋሪ ቸክ ሂልደብራድት 'ለታንክስጊቪንግ' ወይም ለምስጋና ቀን በዋረን የሚገኘውን የህዝብ ቤተመጽሃፍ በጎበኘበት ወቅት "ቤዝ ቦል ዛኒየስት ስታር" የሚል ርዕስ ያለው መጽሃፍ ይዞ ሄዶ ሳይመልስ ቀርቷል።
"ብዙ መጻህፍት በሚኖርህ ጊዜ እያንዳንዱን መጻሃፍ አታይም። ሳጥን ውስጥ ወርውረኻቸው ትሄዳለህ" ሲሉ በበርካታ ከተሞች የኖረው ሂልደብራድት ተናግሯል።
"ነገርግን ከአምስት ወይም ስድስት አመታት በፊት የመጻህፍት መደርደሪያየን ሳገላብጥ የደዊይ ቤተመጻሃፍ ቁጥር አገኘሁ። ይህ ምንድ ነው?"
በመጽሃፉ ውስጥ ታህሳስ 4፣1974 ለዋረን ቤተመጻህፍ መልስ የሚል ስሊፕ አገኘ።
ሂልደብራንድት ለኤፒ እንደገለጸው መጽሃፉን 50ኛ አመት ልደቱ እስኪደርስ ማቆየቱን እና መመለሱን ተናግሯል። እሱ ይህን ያደረገው ቤተ መጽሃፉ ለረጅም ጊዜ ያልተመለሰ መጽሀፍ ብሎ ይፋ ያደርገዋል ብሎ በማሰቡ ነው።
ሂልደብራንድት የቤተመጽሃፉን ዳይሬክተር አክሳና ኧርበን በቅርቡ አግኝቶ ጉዳዩን ማሳወቁን ገልጿል። ግለሰቡ ከእዚያ ወዲህ ምንም የሰማው ነገር አለመኖሩን ቢገልጽም ኧርበን ለዴትሮይት ፍሪ ፕረስ እንደተናገሩት ለሁሉም ነገር ይቅርታ ተደርጎለታል።
"የተወሰኑ ሰዎች ደፍረው መጽሃፍ ለመመለስ አይመጡም" ብለዋል ዳይሬክተሯ።
"መጽሃፉ እና ግለሰቡ ከሲስተም ስለጠፉ ምንም የሚያስቀጣው ነገር የለም።"
ስለዚህ 'ቤዝ ቦል ዛኒየስት ስታርስ' የተባለው መጽሀፍ በድጋሚ መደርደሪያ ላይ ይቀመጣል። ሂልደብራንድት በምላሹ አሁን ላይ 'ማንበብ መሰረታዊ' ነው ለተባለ ለትርፍ ላልተቋቋመ ድርጅት መጽሃፉን ባለመመለሱ ምክንያት ለ 5ዐ አመታት ያህል ከተጠራቀመው ቅጣት ጋር እኩል የሚሆን 4564 ዶላር ለማሰባሰብ እየሞከረ ነው ተብሏል።