በታህሳስ 9 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ የሶስት ብር ቅናሽ አድርጓል
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ25 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የታህሳስ 9 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ የሶስት ብር ቅናሽ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.2433 ብር ገዝቶ በ123.6682 ብር እየሸጠ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
ኦሮሚያ ባንክ ከ20 ቀናት በፊት ያወጣውን ምንዛሬ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ124.7099 ብር በመግዛት በ127.2041 ብር በመሸጥ ላይ ነው።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.6487 ብር ገዝቶ በ127.1417 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክም በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላር በ124.7392 ብር ገዝቶ በ127.2340 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ነው በእለታዊ ተመኑ ላይ ያመላከተው።