ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ ኔቶን ለመዋጋት መዘጋጀት አለባት ሲሉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
መከላከያ ሚኒስትሩ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያሉት ወታደራዊ እቅዶች ሞስኮ በሚቀጥሉት አመታት ለጦርነት መዘጋጀት እንዳለባት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል
የጦር ግንባር ሁኔታዎችን የሚተነትነው ኦፕን ሶርስ ማፕስ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ የሩሲያ ጦር ከ2022 ወዲህ በከፍተኛ ፍጥነት በመገስገስ ላይ ይገኛል
ሩሲያ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ውስጥ ኔቶን ለተናገሩ። መዘጋጀት አለባት ሲሉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሩሲያ በሚቀጥለው አስር አመት በአውሮፓ ያለውን የኔቶ ጥምረት ለመዋጋት መዘጋጀት እንዳለባት በትናትናው እለት የገለጹ ሲሆን ፕሬዝደንት ፑቲን ደግሞ የዩክሬን ጦርነት ሞስኮ በምትፈልገው መልኩ እየሄደ ነው ብለዋል።
የፑቲን መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቮ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ያሉት ወታደራዊ እቅዶች ሞስኮ በሚቀጥሉት አመታት ለጦርነት መዘጋጀት እንዳለባት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
"የመከላከያ ሚኒስቴር ተግባራት ከኔቶ ጋር ሊኖር የሚችልን ቀጥተኛ ግጭት ጨምሮ በመካከለኛ ጊዜ ሊከሰቱ ለሚችሉ ማንኛውንም ቢሆኖች ላይ መሰረት ያደረጉ ናቸው" ሲሉ ቤሎሶቭ ፑቲን ጨምሮ በመስሪያ ቤታቸው በተሳተፉበት ስብሰባ ተናግረዋል።
ቤሎሶቭ በቀጣይ ለሚኖሩ ግጭቶች ያስፈልጋሉ ያሏቸውን ማሻሻያዎች አድርገዋል። ቤሎሶቮ አሜሪካ የኑክሌር ኃይሏን ዘመናዊ ለማድረግ፣ በፖላንድ የሚሳይል ሰፈር ለማቋቋም፣ በ2026 የመካከለኛ ርቀት ሚሳይሏን ወደ ጀርመን ለመላክ የያዘቻቸው እቅዶች ወደፊት ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
አሜሪካ ሞስኮ በስምንት ደቂቃ ውስጥ የሚደርስ ሀይፐርሶኒክ ሚሳይል በቅርቡ ሊኖራት ይችላል ብለዋል ቤሎሶቮ።
ፑቲን በዚሁ ስብሰባ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በጎ ፈቃደኛ ዘማቾች መመልመላቸው ጦርነቱ በሩሲያ የበላይነት እንዲመራ አድርጓል ብለዋል። የጦር ግንባር ሁኔታዎችን የሚተነትነው ኦፕን ሶርስ ማፕስ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ የሩሲያ ጦር ከ2022 ወዲህ በከፍተኛ ፍጥነት በመገስገስ በርካታ የዩክሬን ቦታዎችን እየተቆጣጠረ ይገኛል።
"የሩሲያ ጦር በሁሉም ግንባሮች ወጥረው እየተዋጋ ነው።በዚህ አመት ብቻ 189 መንደሮችን ተቆጣጥሯል" ብለዋል ፑቲን።
ፑቲን በዚህ አመት 430 ሺ በጎፈቃደኞች ወደ ጦሩ መቀላቀላቸውን እና ይህ ቁጥር ባለፈው አመት ከነበረው 300 ሺ ገደማ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
ቤሎሶቭ እንደገለጹት ሩሲያ የዩክሬን ኃይሎችን በቀን 30 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ በማስለቀቅ በዚህ አመት 4500 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ይዛለች።
ምዕራባውያን ሩሲያን ወደ ቀይ መስመሮቿ እየገፏት ነው ሲሉ የሚከሱት ፑተን ሞስኮ እንደማትታገስ እና ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።