ከኢራን የስለላ ኤጀንት ጋር ግንኙነት አድርጓል የተባለ እስራኤላዊ ታሰረ
ተጠርጣራው አሁን ላይ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ክስ ይመሰረትበታል ተብሎ እንደሚጠቅም ተገልጿል
እስራኤል እና ኢራን አንዳቸውን ሌላኛቸውን ለመሰለል ተሰማርተዋል ያሏቸውን ግለሰቦች በመያዝ ይፋ ያደርጋሉ
ከኢራን የስለላ ኤጀንት ጋር ግንኙነት አድርጓል የተባለ እስራኤላዊ ታሰረ።
ከኢራን የስለላ ኤጀንቶች ጋር ግንኙነት አድርጎ ክፍያ ለመቀበልና በምላሹ ጥቃት ለመፈጸም አሲሯል በሚል የተጠረጠረው እስራኤላዊ የእየሩሳሌም ነዋሪ መያዙን የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች በትናንትናው አስታውቀዋል።
የሽንቤት የደህንነት አገልግሎት እና የእስራኤል ፖሊስ ቃል አቀባዮች ባወጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት የ23 አመቱ ግለሰብ "ጆን" ከተባለ የኢራን ኤጀንት ጋር ባለፈው ጥቅምት ግንኙነት በማድረግ እና የጸጥታ ችግር በመፍጠር ተጠርጥሮ በህዳር ወር በቁጥጥር ሰር ውሏል።
መግለጫው እንዳለው ምርመራው ግለሰቡ የእየሩሳሌምን የቀላል ባቡር የኤሌክትሪክ ሲስተም ለመቁረጥ ማቀዱን እና የኃይል አቅርቦቱ ያለበትን ቦታ የሚያሳይ ቪዲዮ ለኢራኑ ኤጀንት መላኩን ያሳያል።
ግለሰቡ በእስራኤል ላይ ጥቃት ለመፈጸም መሳሪያ፣ ሳይለንሰር እና ተቀጣጣይ መሳሪያዎችን ለመግዛት እያፈላለገ ነበር ብሏል መግለጫው።
ተጠርጣራው አሁን ላይ ታስሮ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ክስ ይመሰረትበታል ተብሎ እንደሚጠቅም ተገልጿል።
እስራኤል እና ኢራን አንዳቸውን ሌላኛቸውን ለመሰለል ተሰማርተዋል ያሏቸውን ግለሰቦች በመያዝ ይፋ ያደርጋሉ።
በእስራኤልና ኢራን መካከል የነበረው የበርካታ አስርት አመታት ፍጥጫ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር የፍልስጤሙ ሀማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል።
እስራኤል ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ጸረ-እስራኤል ታጣቂዎችን ታስታጥቃለች የሚል ተደጋጋሚ ክስ ታቀርባለች።
ቴህራን ውስጥ በእንግድነት ለተገኙት የሀማስ የፖለቲካ መሪ መገደል እስራኤልን ተጠያቂ ያደረገችው ኢራን በእስራኤል ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀጥተኛው ጥቃት ፈጽማለች።እስራኤልም የአጸፋ ምላሽ ስጥታለች።ሁለቱ ሀገራት አሁንም ፍጥጫ ውስጥ ይገኛሉ።