በታህሳስ 12 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ ከ278 ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ የታህሳስ 12 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ጎህ ቤቶች ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር እየገዛ በ127.3679 ብር እየሸጠ መሆኑን እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ ጠቁሟል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8043 ብር ገዝቶ በ127.3004 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ባለፈው ሳምንት ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ ነው።