ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ከሶሪያ መሪዎች ጋር ለመነጋገር በደማስቆ እንደሚገኙ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
በ2012 አሜሪካ በደማስቆ ያላትን ኢምባሲ በመዝጋት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋርጣ ነበር
አሜሪካ የአሳድን አስተዳደር እንዲያስወግድ እና እስላማዊ የሸሪዓ ህግን በሶሪያ እንዲያቋቋም አልቃኢዲ ስራ ሰጥቶታል በሚል ነበር በ2013 ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችው
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን በሀያት ታህሪር አል ሻም(ኤችቲኤስ) ከሚመሩት የሶሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመመከር በዛሬው እለት ደማስቆ መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቋል።
የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ዋነኛ ዲፕሎማት ባርባራ ሊፍ፣ የሆስቴጅ ጉዳይ ፕሬዝደንታዊ ተወካይ ሮገር ካርስቴንስ፣ በቅርቡ የሶሪያን ጉዳይ እንዲከታተሉ የተሾሙት ከፍተኛ አማካሪ ዳኒኤል ሩቢንስተን ሶሪያን ለረጅም ጊዜ የመራው በሽር አላሳድ በተቃዋሚ ታጣቂዎች ከስልጣን ከተገረሰሰ በኋላ ደማስቆን የጎበኙ የመጀመሪያዎቹ ዲፕሎማቶች ሆነዋል።
ይህ ጉብኝት የተካሄደው ምዕራባውያን ሀገራት ቀስ በቀስ በራቸውን እየከፈቱ እና በቡድኑ ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ፍረጃ ስለማንሳት ወይም ስላለማንሳት እየተወያዩ ባለበት ወቅት ነው። የአሜሪካ የሉእካን ቡደን ጉብኝት ቡድኑ በቅርቡ ከፈረንሳይ እና እንግሊዝ ጋር ግንኙነት ማድረጉን ተከትሎ የመጣ ነው።
የአማሪካ ባለስልጣናት ከኤችቲኤስ ተወካዮች ጋር በሚኖራቸው ቆይታ አካታችነትን እና የአናሳዎች መብት መከበርን ጨምሮ በርካታ መርሆች በሶሪያ ሽግግር ውስጥ እንዲካተቱ ወይይት እንደሚያደርጉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። የልኡክ ቡድኑ በ2012 ወደ ሶሪያ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ስለታሰረው የአሜሪካ ጋዜጠኛ ኦስቲን ታይስ አዲስ መረጃ ለማግኘት ይጥረሉ ተብሏል።
ቃል አቀባዩ " የሲቪል ማህበረሰብን አባላትን፣ አክቲቪስቶችን፣ የተለዩ የማህበረሰብ አባላትን እና ሌሎች የሶሪያ ድምጾችን ጨምሮ ሶሪያውያንን ስለሀገራቸው የወደፊት እጣፋንታ እና አሜሪካ እንዴት ልትረዳቸው እንደምትችል በቀጥታ ወይይት ያደርጋሉ"ብለዋል።
ቃል አቀባዩ አክሎም እንደገለጸው የልኡክ ቡድኑ በአሜሪካና በቀጣናው አጋሮቿ ጆርዳን ውስጥ ስለጸደቀው የሽግግር መርሆች ከኤችቲኤስ ተወካዮች ጋር ይገናኛሉ።
በ2012 አሜሪካ በደማስቆ ያላትን ኢምባሲ በመዝጋት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋርጣ ነበር።
በኤችቲኤስ የሚመሩት ታጣቂ ቡድኖች በፈጸሙት ጥቃት በጥቂት ቀናት ውስጥ ለ 50 አመታት ያህል የቆየውን የአሳድን እና ቤተሰቦቹን አገዛዝ መገርሰስ ችለዋል። ነገርግን ታጣቃዎቹ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ያደርጉ ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
አሜሪካ የአሳድን አስተዳደር እንዲያስወግድ እና እስላማዊ የሸሪዓ ህግን በሶሪያ እንዲያቋቋም አልቃኢዲ ስራ ሰጥቶታል በሚል ነበር በ2013 ሽብርተኛ ብላ የፈረጀችው። ከአሜሪካ በተጨማሪ ቱርክ፣ የአውሮፓ ህብረት እና ተመድም በድኑን በሽብርተኝነት ፈርጀውታል።