በታህሳስ 16 2017 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች በዶላር መግዣ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርገዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላርን በ123 ብር ገዝቶ በ126 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8055 ብር ገዝቶ በ127.3016 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጎህ ቤቶች ባንክ ከ22 ቀናት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር በመግዛት በ127.3679 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክ የታህሳስ 16 2017 የውጭ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.8450 ብር ገዝቶ በ127.3419 ብር እየሸጠ ነው።