በሶሪያ የገና ዛፍ መቃጠሉን ተከትሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ
አንድ ፊቱን የሸፈነ ታጣቂ ክርስቲያኖች በብዛት በሚገኙበት ማዕከላዊ ሶሪያ የተቀመጠ ግዙፍ የገና ዛፍን በእሳት ሲያቀጣጥል በተንቀሳቃሽ ምስል ታይቷል
ተቃዋሚዎቹ አዲሱ በመቋቋም ላይ የሚገኘው መንግስት አነሳ ቁጥር ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል
በሶሪያ በሀማ ከተማ አቅራቢያ በአደባባይ ላይ የተቀመጠ የገና ዛፍ መቃጠሉን ተከትሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡
በርካታ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሚኖሩበት ሱካለቢያ በተባለ ማዕከላዊ የሶሪያ ከተማ የበዓሉን መቃረብ ተከትሎ የተሰቀለው የገና ዛፍ ፊቱን በጭንብል በሸፈነ ታጣቂ በእሳት ሲቀጣጠል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ታይቷል፡፡
ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድን ከስልጣን ያስወገደውን ውጊያ የመራው አማጺ ቡድን ቃጠሎውን የፈጸሙት ሰዎች የውጭ ተዋጊዎች መሆናቸውን በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እና ዛፉ በፍጥነት እንደሚጠገን ተናግሯል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች ድርጊቱ በተፈጸመበት ሱካለቢያ እና ሌሎች የሶሪያ አካባቢዎች በመውጣት አዲሱ አስተዳደር ለአናሳ የማህበረሰብ ክፍሎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
በዋና ከተማዋ ደማስቆ ለተቃውሞ የወጡ የእምነቱ ተከታዮች መስቀል እና የሶሪያን ባንዲራ በመያዝ ለመስቀላችን እንሞታለን የሚሉ መፈክሮችን አንግበው ታይተዋል፡፡
ከኤፍፒ ጋር ቆይታ ያደረገ አንድ ሰልፈኛ እምነታችንን በነጻነት ማንጸባረቅ የማንችል ከሆነ እዚህ ምንም አንሰራም ሲል ተናግሯል፡፡
ሶሪያ የበርካታ ጎሳ እና ሀይማኖት ቡድኖች መገኛ ናት። ከነዚህም መካከል ኩርዶች፣ አርመኖች፣ አስራውያን፣ ክርስቲያኖች፣ ድሩዜ፣ አላዊት ሺዓ እና የአረብ ሱኒዎች የሚጠቀሱ ሲሆን አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ህዝብ ነው።
ምዕራባውያንን ጨምሮ በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የመብት ተሟጋቾች አዲስ የሚዋቀረው መንግስት የሁሉንም ሶሪያውን እና እምነት ተከታዮች መብት እንዲያከብር እየተጠየቀ ይገኛል፡፡
ከዚህ ባለፈም አዲሱ መንግስት ከሀይማኖታዊ መንግስት ተላቆ ነጻ መንግስት እንዲያቋቁም አሜሪካ እና ምዕራባውያን ጫና ማሳደራቸውን ጠይቀዋል፡፡