የሩሲያ መርከብ በሜዲትራኒያን ባህር መስጠሟን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
በ 2009 የተገነባችው መርከቧ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አካል በሆነው ኦቦሮኖሎጂስቲካ ኩባንያ ስር ነበር የምትተዳደረው።
መርከቧ ሁለት ግዙፍ የወደብ መርከቦችን ይዛ ወደ የሩሲያዋ ሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላዲቮስቶክ እያመራች ነበር ተብሏል
በሞተር ክፍል መፈንዳት ምክንያት "ኡርዛ ማጆር" የተባለችው የሩሲያ የጭነት መርከብ በሜዲትራኒያን ባህር በስፔን እና አልጄሪያ መካከል መስጠሟን እና ሁለት ሰራተኞቿ መጥፋታቸውን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው እለት አስታውቋል።
በ 2009 የተገነባችው መርከቧ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አካል በሆነው ኦቦሮኖሎጂስቲካ ኩባንያ ስር ነበር የምትተዳደረው።
ቀደም ሲል ኩባንያው መርከቧ ሁለት ግዙፍ የወደብ መርከቦችን ይዛ ወደ የሩሲያዋ ሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላዲቮስቶክ እያመራች ነበር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ የቀውስ ክፍል ባወጣው መግለጫ ከ 16ቱ የመርከቧ ሰራተኞች ውስጥ 14 ከአደጋው መትረፋቸውን እና ወደ ስፔን መወሰዳቸውን የገለጸ ሲሆን ሁለት ሰራተኞች ግን እስካሁን የደረሱበት አልታወቀም ብሏል።
መግለጫው ፍንዳታው በምን ምክንያት እንደተከሰተ አልገለጸም።
የመርከቧ ባለቤት ከአራት ቀናት በፊት በቭላዲቮስቶክ ወደብ የሚተከሉ የተለዩ ክሬኖችን እና በርዶ መስበሪያዎችን ጭና ነበር።
የመርከቧ የመከታተያ መረጃ መርከቧ ከሩሲያ ሴንትፒተርስበርግ ታህሳስ 11፣2024 መነሳቷን እና ሰኞ እለት በአልጄሪያ እና ስፔን ሆና የመጨረሻ ምልክት መስጠቷን ገልጿል።
ሮይተርስ የስፔኑን ኢል ስፓኞል የተባለውን የዜና ድረ ገጽ ጠቅሶ እንደዘገበው ሰራተኞቹ የስፔን ባህር ኃይልን ጨምሮ በርካታ ቡድኖች በተሳተፉበት የነፍስ አድን ስራ ወደ ስፔኗ ወደብ ካርታገና ማውጣት ተችሏል። የባህር ኃይል መርከብ ሰራተኞቹን በማዳን ጥረት ተሳትፋለች። የሰጠመችው መርከብ ጥር 22፣2024 ቭላዲቮስቶክ ትደርሳለች ተብሎ ነበር።