የግል ንግድ ባንኮች በዶላር መግዣ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርገዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዶላር መግዣ እና መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.4220 ብር ገዝቶ በ126.9165 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ ምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ጎህ ቤቶች ባንክ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር በመግዛት በ127.3679 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ጸደይ ባንክ የታህሳስ 16 2017 የውጭ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.8462 ብር ገዝቶ በ127.3432 ብር እየሸጠ ነው።