ሰሜን ኮሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ሶማሊያ እና አልጀሪያ በዓሉ ከማይከበርባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው
የገና በዓል የማይከበርባቸው ሀገራት እነማን ናቸው?
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የእየሱስ ክርስቶስ ልደትን በማስመልከት የሚከበረው የገና በዓል በመላው አለም ከሚከበሩ ሀይማኖታዊ ክብረ በአሎች መካከል አንዱ ነው፡፡
የበዓሉ አከባበር ከሀገር ሀገር የሚለያይ ሲሆን የተወሰኑ ሀገራት ደግሞ ዕለቱን እንደ ማንኛውም ቀን በስራ ያሳልፋሉ፡፡
በዓሉ ከማይከበርባቸው ሀገራት መካከል ሰሜን ኮሪያ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ አልጀሪያ እና ሶማልያ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በገና ዛፍ መኖርያቤቶችን እና መንገዶችን ማሸብርቅ ፣ ስጦታ እና የመልካም ምኞት መግለጫ ካርዶችን መለዋወጥ በርካታ የክርስትና እምነት ተከታዮች የገና አከባበር ከሚመሳሰሉባቸው መገለጫዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡