የጀርመኑ መሪ ሽሎዝ ከፑቲን ጋር ያደረጉትን ንግግር ተገቢ ነው ሲሉ ተከራከሩ
ሽሎዝ ከፍተኛ ትችት የቀረበበትን ወደ ክሬሚሊን የመደወል ውሳኔን ተገቢ ነው ብለዋል
የጀርመኑ መሪ ኦላፍ ሽሎዝ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ባደረጉት ንግግር ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ባለው ጦርነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አለማሳየታቸውን ተናግረዋል
የጀርመኑ መሪ ሽሎዝ ከፑቲን ጋር ያደረጉትን ንግግር ተገቢ ነው ሲሉ ተከራከሩ።
የጀርመኑ መሪ ኦላፍ ሽሎዝ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ባደረጉት ንግግር ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን እያደረገች ባለው ጦርነት ዙሪያ የአቋም ለውጥ አለማሳየታቸውን ተናግረዋል።
ሽሎዝ ከፍተኛ ትችት የቀረበበትን ወደ ክሬሚሊን የመደወል ውሳኔን ተገቢ ነው ብለዋል።
በሁለት አመት ውስጥ ከፑቲን ጋር አንድ ሰአት የቆየ ውይይት ያደረጉት ተቀባይነታቸው ዝቅተኛ የሆነው ሽሎዝ የሚፈተኑበት አካባቢያዊ ምርጫ ሶስት ወር ይቀረዋል።
የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪን ጨምሮ ተችዎች ሽሎዝ ለሀገር ውስጥ የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ ምዕራባውያን ለዩክሬን ያላቸውን አጋርነት የሚያፈርስ ተግባር ነው ብለዋል።
ሽሎዝ እንዳሉት "ፑቲን ከጀርመን፣ አውሮፓ እና ከተቀረው አለም ድጋፍ አገኛለሁ ብለው እንዳይተማመኑ መናገር ያስፈልጋል።"
"ውይይቱ በዝርዝር የተካሄደ ነው። ነገርግን የሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ስለጦርነቱ ያላቸውን አቋም አልቀሩም፤ ይህ ጥሩ ዜና አይደለም" ብለዋል ሽሎዝ።
የስልክ ንግግሩ በሩሲያ እና በምዕራባውያን መሪዎች መካከል ያለው ግንኙነት የመሻሻል ምልክት እያሳየ እና ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ወደፊት እየገፋች ባለችበት ወቅት የተካሄደ ነው።
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ቀደም ሲል የኔቶ አባል የሆነችው ፖርቹጋል ጠቅላይ ሚኒስትር በሩሲያ በተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ላይ መገኘታቸው በዩክሬን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ማስነሳቱ ይታወሳል።
በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ የዩክሬን ጦርነት በፍጥነት እንደሚያስቅሙት እየተናገሩ ሲሆን ከቀድሞቹ ይልቅ ለሞስኮ በጎ አተያይ ያላቸው የካቢኔ አባላትን ሾመዋል።
ሾሎዝ እንዳሉት ከሆነ ይህ ለአውሮፓ ጥሩ አይደለም።