እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ70 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ ቢያንስ ስድስት ቤተሰቦች በህንጻው ላይ ይኖሩ ነበር
ኳታር "ፍቃደኝነታቸውን" እስከሚያሳዩ ድረስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ የምታደርገው የማደራደር ጥረት ማቆሟን ለሀማስ እስራኤል አሳውቃቸዋለች
እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ከ70 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
እስራኤል በጋዛዋ ቤት ላሂያ ግዛት በሚገኝ ባለብዙ ፎቅ የመኖሪያ ህንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የፍልስጤም የሲቪል ኢመርጀንሲ አገልግሎት በህንጻው ውስጥ 70 ገደማ ሰዎች ይኖሩ እንደነበር ገልጿል።
በሀማስ የሚተዳደረው ሚዲያ የሟቾቹን ቁጥር 72 አድርሷቸዋል። የጤና ባለሙያዎች እና ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ ቢያንስ ስድስት ቤተሰቦች በህንጻው ላይ ይኖሩ ነበር።
እስራኤል በዚህ ጉዳይ እስካሁን ያለችው የለም። እስራኤል ሁል ጊዜ የሀማስን የሚዲያ ቢሮ የሟቾችን ቁጥር በማጋነን ትከሰዋለች። ሮይተርስ አገኘሁት ባለው ቪዲዮ የአካባቢው ሰዎች አስከሬኖችን ከፍርስራሾቹ ውስጥ ሲያወጡ እንደሚታዩ ገልጿል።
የእስራኤል ጦር ሀማስ መልሶ እንዳይደራጅ እና ጥቃት እንዳይፈጽም በሚል ምክንያት ነበር ባለፈው ወር በቤት ላሂያ እና በአቅራቢያዋ በሚገኙት ቤይት ሀኖን እና ጃባሊያ ታንኮቹን ያስገባው።
ጦሩ እንደገለጸው ከሆነ በእነዚህ ቦታዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ገድሏል።
የሀማስ አጋር የሆነው እስላማዊ ጅሀድ በዛሬው እለት ያወጣው መግለጫ ተዋጊዎቹ በቤይት ላሂያ በነበረው ውጊያ የእስራኤልን ታንክ አቃጥለዋል። በዚህ መረጃ ጉዳይ የእስራኤል ጦር ያለው የለም።
በዛሬው እለት ጠዋት እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው ቡረጂ ካምፕ ላይ ያስወነጨፈችው ሚሳይል መኖሪያ ቤት ላይ አርፎ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል። ባለሙያዎቹ አክለውም እንደገለጹት በቅርቡ ርቀት በሚገኘው ኑሰራት ካምፕ ላይ በደረሰ ጥቃት አራት ሰዎች ተገድለዋል።
ኳታር "ፍቃደኝነታቸውን" እስከሚያሳዩ ድረስ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾች እንዲለቀቁ የምታደርገው የማደራደር ጥረት ማቆሟን ለሀማስ እስራኤል አሳውቃቸዋለች።
ሁለቱ ተዋጊ ኃይሎች እርስበእርስ መካሰሳቸውን ቀጥለዋል።
ሀማስ ጦርነቱን በዘላቂነት ለማስቅም የሚያስችል ስምምነት እንደሚፈልግ የገለጸ ሲሆን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደግሞ ጦርነቱ የሚቆመው ሀማስ ሲጠፋ ብቻ ነው የሚል አቋም ይዘዋል።
ሀማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 1200 ሰዎች መግደሉን እና ሌለች 250 የሚሆኑን አግቶ መወሰዱን ተከትሎ እስራኤል እየሰወደች ባለው መጠነሰፊ ጥቃት እስካሁን የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ43ሺ አልፏል።