መሐመድ አፊፍ የሄዞላህ የረጅም የሚዲያ አማካሪና ኃላፊ ነበሩ
የሊባኖስ ሄዝቦላህ ቡድን የረጅም ጊዜ የሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት መሐመድ አፊፍ በቤቱት በተፈጸመ ጥታት መገደሉ ተገለፀ።
ሮይተርስ የሊባኖስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ባወጣው ዘገባው፤ መሐመድ አፊፍ በማዕከላዊ ቤሩት በሚገኘው የአረብ ሶሻሊስት ባዝ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ላይ በተፈፀመ ጥቃት ነው የተገደሉት።
መሐመድ አፊፍ በእስራኤል የተገደሉት የሄዞላህ መሪ የነበሩት ሀሰን ነስረላህ የረጅም ጊዜ የሚዲያ አማካሪና የቡድኑ የሚዲያ ኃላፊ ነበሩ።
ኃፊው መሐመድ አፍፊ ባሳለፍነው ሳምንት ለመጨረሻ ጊዜ በቤሩት የሚገኙ ጋዜጠኞችን ሰብስበው ስለ ጦርነቱ መግለጫ መስጠታቸውም ተነግሯል።
አፊፍ ከአማካሪነት በተጨማሪም የሄዝቦላህ አል ማነር ቴሌቪዥንን ለረጅም ጊዜ በመምራም ይታወቃሉ።
በሄዝቦላህ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ካነጣጠሩት የእስራኤል ጥቃቶች መሐማድ አፊፍ በቅርቡ የተከገደሉት ውስጥ ከፍተኛው አመራ ናቸው።
እስራኤል በቤሩት ደቡባዊ ክፍፍ የሄዝቦላህ አመራችን ኢላማ በማድረግ በፈጸመቻቸው ጥቃች የቡድኑ መሪ ሀሰን ነስረላህን ጨምሮ፣ ተተኪ አመራር እንደሚሆኑ የሚጠበቁትን አመራች ጭምር መግደሏ ይታወሳል።