በህዳር 13 የባንኮች የምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 123 ብር ገዝተው እስከ 126 ብር እየሸጡ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ123.8506 ብር እየገዛ በ126.3276 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አቢሲኒያ ባንክ የትናንቱን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሎ አንድ ዶላርን በ122.8540 ብር እየገዛ በ125.3111 ብር እየሸጠ ነው።
ጎህ ቤቶች ባንክ የህዳር 13 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.9225 ብር በመግዛት በ125.3810 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በበኩሉ አንድ የአሜሪካ ዶላርን 121.2433 ብር እየገዛ 123.6682 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን አመላክቷል።