በባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ ነው
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከሁለት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ቅዳሜ እለት ያወጣውን ያውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬ ህዳር 16 2017 አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.6459 ብር ገዝቶ በ126.1188 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ብርሃን ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ አንድ ዶላርን በ123.4517 ብር ገዝቶ በ125.9207 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ጠቁሟል።
ጎህ ቤቶች ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.9225 ብር ገዝቶ በ125.3810 ብር እየሸጠ ይገኛል።