በብሪታንያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ማዘዣ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ድሮኖች ታዩ
እስካሁን ድሮኖቹ የማን እንደሆኑ እና ከየት እንደመጡ እስካሁን አልታወቀም
የአሜሪካ ጦር ማዘዣው ኤፍ 15 የጦር አውሮፕላኖችን ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያን ያያዘ ነው
በብሪታንያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ማዘዣ ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ድሮኖች ታዩ፡፡
ዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ አውሮፓን ጨምሮ በበርካታ የዓለማችን ሀገራት የጦር ማዘዣዎች አሏት፡፡
በብሪታንያ ኖርፊክ ባለው ዘመናዊ ጦር ማዘዣ ባሳለፍነው ረቡዕ እና አርብ ዕለታት ሶስት ድሮኖች በድንገት ታይተዋል፡፡
እነዚህ ሮቦቶች ለምን ዓላማ እና ማን እንደላካቸው እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን የብሪታንያ መከላከያ እና የአሜሪካ ጦር በጉዳዩ ዙሪያ የጋራ ምርመራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የበእንግሊዝ ያለው የአሜሪካ ጦር ማዘዣ በአውሮፓ ካሉ የጦር ማዘዣዎች መካከል አንዱ ሲሆን ኤፍ-15ን ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች የሚገኙበት ነው ተብሏል፡፡
በማዘዣው ላይ በድንገት ታዩ የተባሉት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ይመቱ አይመቱ እስካሁን በይፋ አልተገለጸም፡፡
የብሪታንያ ወንጀል ሚኒስትር ስለ ወንጀል መጨመር መግለጫ እየሰጡ እያለ የእጅ ቦርሳቸው ተሰረቀ
ከዚህ በተጨማሪም ድሮኖቹ በጦር ማዘዣው ላይ ያደረሱት ጉዳት ስለመኖሩም በአሜሪካም ሆነ በብሪታንያ ጦር የተገለጸ ነገር የለም፡፡
የአሜሪካ ጦር በአውሮፓ ቃል አቀባይ እንዳሉት ሶስት ድሮኖች ብሪታንያ ባለው የጦር ማዘዣዎች ላይ መታየታቸውን አረጋግጠዋል፡፡
የብሪታንያ መከላከያ ቃል አቀባይ በበኩላቸው በአሜሪካ ጦር ማዘዣ አቅራቢያ የታዩት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ዋነኛ ስጋት መሆናቸውን ገልጸው ማዠዣውን ጨምሮ በውስጥ ያሉ የሰው ሀይሎችን እና የጦር መሳሪያዎችን ደህንነት ጥብቅ ጥበቃ በመደረጋ ላይ መሆኑንም አክለዋል፡፡