በህዳር 19 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ ነው
የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ122 እስከ 124 ብር መግዣ ከ124 እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከአራት ቀናት በፊት ያወጣውን ዋጋ አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.5986 ብር እየገዛ በ125.0506 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ ቅዳሜ ህዳር ህዳር 14 2017 ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ቢያስቀጥልም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ጸደይ ባንክ የህዳር 19 2017 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ በሳንቲሞች ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.4521 ብር ገዝቶ በ126.9411 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ የትናንቱን የምንዛሬ ተመን ስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.1965 ብር ገዝቶ በ126.6805 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትንና የሚሸጥበትን እለታዊ ተመን ይፋ ሲያደርግ አንድ ዶላርን በ123.8647 ብር ገዝቶ በ126.3420 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።