አሜሪካ በእስያ ሚሳኤል ካሰፈረች ሩሲያ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች
አሜሪካ በጃፓን የመካከለኛ እና የአጭር ርቀት ሚሳኤል ልታሰፍር እንደምትችል ከሰሞኑ ተገልጿል
ግማሽ አካሌ በእስያ ይገኛል የምትለው ሩሲያ ጉዳዩ ዋነኛ የደህንነት ስጋት ይደቅንብኛል ብላለች
አሜሪካ በእስያ ሚሳኤል ካሰፈረች ሩሲያ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች፡፡
ባሳለፍነው እሁድ የጃፓን ዜና አገልግሎት አሜሪካ እና በጃፓን ሚሳኤል የማስፈር ፍላጎት እንዳላት ዘግቧል፡፡
አሜሪካ በጃፓን ሶት ቦታዎች በተለይም በናንሴ ወደብ ፣ካጎሺማ እና ኦኪናዋ ቦታዎች ላይ ሚሳኤል የማስፈር እቅድ አላት ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሌላኛዋ የእስያ ሀገር ፊሊፒንስ አጭር እና መካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን የማጥመድ እቅድ እንዳላትም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይህን ተከትሎ ሩሲያ በቶኪዮ እና ዋሸንግተን እቅድ እንደሚያሳስባት አስታውቃለች፡፡
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛራኮቫ እንዳሉት አሜሪካ በጃፓን ሚሳኤል ማስፈሯ በሩሲያ ላይ የደህንነት ስጋት ይደቅናል ብለዋል፡፡
ሩሲያ ቁርዓንን አቃጥሏል ያለችውን ሰው በ14 ዓመት እስር ቀጣች
የሩሲያ ግማሽ አካል በእስያ የሚገኝ ነው ያሉት ቃል አቀባይዋ አሜሪካ ያቀደችውን ካደረገች ሩሲያም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድም ተናግረዋል፡፡
ቃል አቀባይዋ አክለውም ጃፓን ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ ያሳሰቡ ሲሆን ቶኪዮ የሩሲያን ማስጠንቀቂያ ችላ ብላ አሜሪካ ሚሳኤል ካጠመደች የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን ብለዋል፡፡
አሜሪካንን ጨምሮ የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያዎች መስጠታቸውን ተከትሎ የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት መልኩን ቀይሯል፡፡
ሩሲያ ለኔቶ ሀገራት ድጋፍ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ህጓን ያሻሻለች ሲሆን ኦሬሽኒክ የተሰኘውን የመካከለኛ ርቀት አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ወደ ዩክሬን መተኮሷ ይታወሳል፡፡