ዛሬ መስከረም 22 በባንኮች 1 ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች 1 ዶላርን እስከ 112 ብር እየገዙ፤ እስከ 126 ብር እየሸጡ ይገኛሉ
ባንኮች አዲስ አመትን አስመልክቶ ከውጭ በሃዋላ ለሚላክ የውጭ ምንዛሬ ያቀረቡት ስጦታ ሊጠናቀቅ 8 ቀናት ቀርተውታል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የ2017 አዲስ ዓመት አስመልክቶም ባንኮች በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያውን በባንኮች አማካኝነት ገንዘብ እንዲልኩ የሚያበረርታታ ተመን እያወጡ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የሚላክን ገንዘብ ከባንኩ ለሚቀበሉ ደንበኞቹ ከዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዶላር ላይ ተጨማሪ 8 ብር ስጦታ እሰጣለሁ ብሏል።
ባንኩ ዛሬ መስከረም 22 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ የሰሞኑን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የምንዛሬ ዋጋ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህም በሃዋላ የሚላክ 1 ዶላርን ከመደበኛው የምንዛሬ ዋጋ ላይ እስከ 16 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ማሳወቁ ይታወቃል።
ባንኩ በመደበኛው የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.5985 ብር እየገዛ በ126.6733 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።
እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።
በዚህም ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ112.4804 ብር እየገዛ በ125.9781 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባወጣው የመስከረም 22 የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላርን በ112.9759 ብር እየገዛ በ126.5330 ብር እየሸጠ መሆኑን ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ዋጋ አንድ ዶላርን በ112.7310 ብር እየገዛ በ123.7200 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ አመላክቷል።