ልጃቸውን በአንድ ሺህ ዶላር ለመሸጥ የተስማሙት ወላጆች
አሜሪካዊያን ጥንዶች የሁለት ወር ልጃቸውን በአንድ ሺህ ዶላር ለመሸጥ ከተስማሙ በኋላ በፖሊስ ተይዘዋል
ወላጆቹ ልጃቸውን ለመሸጥ በተስማሙበት ውል ላይ ህጻኑን መልሶ ለማግኘትም እንዳይሞክሩም ፈርመዋል ተብሏል
ልጃቸውን በአንድ ሺህ ዶላር ለመሸጥ የተስማሙት ወላጆች
በአሜሪካዋ አርካንሳስ ግዛት የሚኖሩት ዳሪያን አርባን እና ሻሌን ኤህለርስ በቅርቡ ነበር የወንድ ልጅ ወላጅ የሆኑት፡፡
እነዚህ ወላጆች የሁለት ወር እድሜ ያለው ወንድ ልጃቸውን በአንድ ሺህ ዶላር ለመሸጥ እንደተስማሙ ተገልጿል፡፡
የ21 እና 20 ዓመት እድሜ ያላቸው ወላጆቹ “እኛ ዳሪየን አረባን እና ሻሌን ኡህለርን የተባል ወላጆች ልጃችንን በአንድ ሺህ ዶላር ለመሸጥ በፈቃዳችን ተስማምተናል” ሲሉ ፊርማቸውን አኑረዋል ሲል ኒዮርክ ፖስት ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የግዢ ስምምነቱ ሀሳብ መቀየር እንዳይኖር ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ፖሊስ ወላጆቹን በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ተገልጿል፡፡
ፖሊስ ስምምነቱ ከተፈጸመበት አካባቢ ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ወደ ወላጆቹ አድራሻ በመሄድ ምርመራ ያደረገ ሲሆን ህጻኑ ከወላጆቹ ተነጥቆ እንክብካቤ ወደሚያገኝበት ማዕከል ገብቷል ተብሏል፡፡
ወላጆቹ ገንዘቡን ከመቀበላቸው እና ህጻኑ ተላፎ ከመሰጠቱ በፊት በቁጥጥርሰ ር ውለዋል የተባለ ሲሆን ጥንዶቹ ከዚህ በፊት የወንጀል ሪከርድ የነበረባው ሆነው ተገኝተዋል፡፡
እነዚህ ወላጆቹ ከዚህ በፊት በቅርቡ የወለዷት ሴት ልጃቸውን ለማሳደግ የገንዘብ እጥረት እንደገጠማቸው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ለቀው እንደነበር ተገልጿል፡፡
ይሁንና ጥንዶቹ ሴት ልጅ ስለመውለዳቸው እስካሁን ማረጋገጫ እንዳልተገኘ በዘገባው ለይ ተጠቅሷል፡፡